በወረዳው ጠቅላላ ምርጫው ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከወጣቶች ጋር ተቀናጅቶ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት አሰታወቀ፡፡
ካነጋገርናቸዉ ነዋሪዎች መካከል ወጣት ኪዳኔ ክንፈና ወጣት ፀጋነሸ አሻ የሃላሌ ከተማ የወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ ሲሆኑ፤ የመራጭነት ካርድ በመውሰድ ጠቅላላ ምርጫው ፍትሐዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የአካባቢውን ሰላም ከማስጠበቅ አኳያ ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በመሆን በየጊዜው ሰፊ ዉይይትና ምክክር በማድረግ ምርጫው ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ወጣቶቹ አሰረድተዋል።
ሌላኛው አሰተያየት ሰጪ ወጣት ደጉ ደኣና ወጣት ያዕቆብ አድማሱ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ላይ በመሳተፍ እንደ ዜጋ ለዲሞክራሲያዊ ባህል ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ድርሻ መወጣታቸውን ተናግረዋል።
ግንቦት 24 በሚካሄደው ቅላላ ምርጫ የመራጭነት ካርድ መያዛቸውን በመግለጽ፤ የወጣቱን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገለጸዋል።
ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ በተለያዩ ዘርፎች ለወጣቶች ግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጥልቀት መሰጠቱን የወረዳው ወጣቶች ክንፍ ኃላፊ አቶ ማርቆስ ኤርጋዶ አሰረድተዋል።
አቶ ማርቆስ አክለውም፤ በአሁኑ ወቅት ወጣቶች በምርጫው በንቃት እንዲሳተፉ ከማድረግ ባለፈ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን እየተወጡ መሆኑን ጠቁመዋል።
በወረዳው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ጋንታ በበኩላቸው፤ የሀገሪቱ የነገ ዕጣ ፋንታ የሚወሰነው በወጣቱ ትውልድ መሆኑን ገልፀው ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን በወረዳ ደረጃ “የወጣቶች ተሳትፎ ለሰላማዊ ምርጫ” በሚል መሪ ቃል ዉይይት ማካሄዱን አሰረድተዋል።
በአካባቢው ሁከት ለመፍጠር አንዳንድ ድብቅ ማንነት በመያዝ በማህበራዊ ሚዲያ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን የማጣራትና ወደ ህግ የማቅረብ ሥራ በስፋት መሰራቱንም ገልጸዋል።
አክለውም፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ወጣቶች ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በማድረግ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ ያሲን ጨተላ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የምረጡን ቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፍ በኣሪ ዞን ጋዘር ከተማ አካሄዱ
በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ እና በላሃ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የማጠቃለያ ሕዝባዊ የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም ተካሄደ
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን 7 ቀናት ብቻ ቀርተውታል