ግንቦት 24 የሚካሄደውን ጠቅላላ ምርጫን ምከንያት በማድረግ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ
“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው የመጨረሻ የሕዝብ ድጋፍና የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ ግብር የተለያዩ የፓርቲው መፈክሮች ተንጸባርቀዋል።
ለታዳሚው የይምረጡን መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባዉዲ፤ በቀጣይ ፓርቲው በጋራ ሀገራዊ አንድነት በኢኮኖሚ ዘርፍ የተሻለች ኢትዮጵያ በመፈጠር በቴክኖሎጂ የታገዘ የፈጠራ ሽግግር ለማድረግ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ራዕዩ፣ ግቡና አጠቃላይ የልማት ውጥኑ ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ማሻገርን ያለመ መሆኑን በንግግራቸው ያነሱት የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ፤ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ደረጃ በደረጃ እየፈታ የሚሄድና ልማት የሚያረጋግጥ ፓርቲ ነው ብለዋል።
የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግሥት ተጠሪ እንዲሁም የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ አቶ አፈዶ ወርቁ በበኩላቸው፤ የብልጽግና ፓርቲ በሀገሪቱ የተሻለ የዲሞክራሲና የፖለቲካ ፉክክር ልምዶችን በማጠናከር ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ እንድትሆንና ጠንካራ የዲፐሎማሲ ሥርዓትን እየገነባ የሚገኝ ፓርቲ ነው ብለዋል።
ከዞኑ ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የንግዱ ማህበረሰብና የከተማ ነዋሪዎች በድጋፍ ሰልፉ የተሳተፉ ሲሆን በግንቦት 24 ምርጫ ካርድ በወሰዱበት ምርጫ ጣቢያ ድምፅ ለመሰጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
በጂንካ ሁለገብ ስታዲየም የተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍና የምርጫ ቅስቀሳ የማጠቃለያ ህዝባዊ ሰልፍ የስፖርታዊ ውድድሮችና ሌሎችም የተለያዩ ሁነቶች የተካሄዱበት ነው።
ዘጋቢ: ጄታ ታገሠ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
55ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ፣ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እየተወጡ መሆናቸውን በወላይታ ዞን የኪንዶ ድዳየ ወረዳ ወጣቶች ገለጹ
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የምረጡን ቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፍ በኣሪ ዞን ጋዘር ከተማ አካሄዱ