ተፈላጊነቱ እየጨመረ የመጣውን የቆጮ ምግብ ጥራትና ተደራሽነት ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎች እያከናወነ መሆኑን በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የብሔራዊ ግብርና ባዮ ቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል ገለጸ
ማዕከሉ የእንሰት ማብላላት ሂደትን ለማፋጠን እና ለማዘመን የሚያስችል የእርሾ ቴክኖሎጂ የማሳያ ፕሮግራም በጉራጌ ዞን እኖር እና ቸሃ ወረዳዎች አካሂዷል።
በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የብሔራዊ ግብርና ባዮ ቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ኢብሳ ፊጤ እንደሚሉት፤ ከእንሰት የተወሰደው የእርሾ ቴክኖሎጂው በአጭር ጊዜ ማብላላት የሚያስችልና ደህንነቱ የተረጋገጠ በመሆኑ አስተዋጽኦው የጎላ ነው።
በማዕከሉ የብሔራዊ ማይክሮቢያል ባዮ ቴክኖሎጂ ምርምር ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ቤተማርያም ከበደ እንደገለፁት፤ ይህ በላብራቶሪ የተረጋገጠው የቆጮ እርሾ ቴክኖሎጂ ቆጮ ተብላልቶ ለምግብነት እስኪደርስ ይፈጅበት የነበረው የ6 ወራት ቆይታ ወደ 28 ቀናት ማሳጠር ያስችላል።
ከዚህ በተጨማሪም ለህብረተሰቡ ጤና የሚጠቅም ተጨማሪ የምግብ ይዘት ያካተተ ነውም ብለዋል።
በጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ የግብርና ኮሙኒኬሽን የስራ ሂደት አስተባባሪ ወ/ሮ ሲሳይ ኮራ በበኩላቸው፤ ቴክኖሎጂው ሽታ አልባ ቆጮን ለማምረት የሚያስችል፣ ቆጮ የሚብላላበት ጊዜን የሚያሳጥር እና ተጨማሪ ንጥረ ነገር ያካተተ በመሆኑ ለውጤታማነቱ ተስፋ ተጥሎበታል ብለዋል።
ወ/ሮ ጌኔ ነስሩ በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ወርቃት ቀበሌ እና ወ/ሮ መቅደስ ጌታሁን በቸሀ ወረዳ ግራር ቀበሌ ያነጋገርናቸው እናቶች ናቸው። በጓሮአቸው የተሞከረው ቴክኖሎጂ ውጤታማነቱን ካረጋገጡ በኋላ እንደሚጠቀሙትና በዚህም ጊዜያቸውን እንደሚቆጥብላቸውና ጥራቱንም እንደሚያሻሽልላቸው ይጠብቃሉ።
ዘጋቢ፡ ተረፈ ሀብቴ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የሀገራችንን ብልፅግና እውን ለማድረግ በበቂ ዕውቀትና ክህሎት የታነፁ ምሁራንን በማፍራት የተሻለ ትውልድ መቅረጽ ቁልፍ ተግባር ነው ሲሉ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) ገለፁ
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል መሆናቸው ከብዙ ህክምና ወጪ የታደጋቸው መሆኑን በወላይታ ዞን የኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ሃላሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተገልጋዮች ተናገሩ
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረው የአህዮች ቀን በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ተከበረ