በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረው የአህዮች ቀን በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ተከበረ
በበዓሉ አህዮች የሚሰጡትን አገልግሎት የሚመጥን እንክብካቤ እና ክብር እንዲያገኙ ለማድረግ ታስቦ መከበሩ ተገልጿል።
የ Donkey Sanctuary የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ፈገግታ ለማ፤ አህዮች የሚሰጡት አገልግሎት ከየትኛውም እንሳስ የሚበልጥ ሆኖ ሳሌ የሚገባቸውን እንክብካቤ ሳያገኙ ሲንቋሸሹ እና ለስድብ ጥቅም ላይ ሲውሉ መቆየታቸውን አውስተዋል።
አህዮች ተገቢውን የጤና እና የመኖ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ከ 30 ዓመት በላይ ድርጅቱ የማስገንዘብ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን አብራርተዋል።
የአስዴፖ MEAN ዳይሬክተር አቶ ወንዶሰን ተረፈ፤ ዝግጅቱ አህዮች የአገልግሎታቸውን ያህል ዋጋ ማግኘት እንዲችሉ የታለመ መሆኑን አስገንዝበው ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
ዶ/ር ሄኖክ ኢብሳ ዋን ዌልፌር ፕሮጀክት አስተባባሪ ሲሆኑ livelihood,welfare እና environmental sanitation ፕሮጀክት ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራባቸው ዘርፎች መሆናቸውን አስረድተዋል።
የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ዳንኤል ደግፌ፤ ዞኑ በርካታ የቁም እንሰሳት እና 139 ሺህ 690 በላይ አህዮች ያሉበት አካባቢ ቢሆንም ከግንዛቤ ክፍተት የተነሳ ትኩረት ተነፍገው መቆየታቸውን ጠቁመው፤ ተገቢውን ክብርና እንክብካቤ በመስጠት ከዘርፉ የሚገኘውን ሁለንተናዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ለህብረተሰቡ ጥሪ አቅርበዋል።
የሳውላ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጌታሁን ኩማ፤ በከተማችን አህዮች ለስቃይና ለእንግልት እንዳይጋለጡ እንደ ዜጋ በባለቤትነት አምባሳደር መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።
በሳውላ ከተማ አህዮቻቸውን በእንክብካቤ በመያዝ ፊት ለወጡ አካላት
ከፕሮጀክቱ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ባገኙት ማበረታቻ መደሰታቸውን ገልፀው ሌሎችም አህዮቻቸውን እንዲንከባከቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡ ሲሳይ አፃ – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)