ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፕሪሚየር ሊጉ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ!
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2025/26 የውድድር ዘመን ማጠቃለያውን ለማድረግ ሲቃረብ፣ ታላቁ የክብር ማዕረግ ወደ ኦልድትራፎርድ አምርቷል።
የማንችስተር ዩናይትዱ የልብ ትርታ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ድንቅ የውድድር ዘመኑ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል።
ቀይ ሰይጣኖቹ ይህንን ክብር ለመጨረሻ ጊዜ ያሸነፉት በ2010/11 የውድድር ዘመን በታላቁ ተከላካያቸው ኔማንያ ቪዲች አማካኝነት ነበር።
ከ15 ዓመታት በኋላ፣ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ያንን የታሪክ አሻራ በድጋሚ አድሶታል።
ብሩኖ ፈርናንዴዝ በውድድር ዘመኑ 20 ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ በማቀበል ሪከርድ መጋራቱ አይዘነጋም።
በተጨማሪም ብሩኖ ፈርናንዴዝ 8 ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።