“የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መባል ስሜቱ የማይታመን ነው!”— ሚኬል አርቴታ
ከ22 ዓመታት ናፍቆት በኋላ መድፈኞቹን ወደ ክብር ማማ ላይ የሰቀለው ስፓኒሻዊው የአርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ፣ የሻምፒዮንነት ስሜቱን በታላቅ አድናቆትና ስሜት ገልጿል።
“የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መባል የማይታመን ስሜት ይፈጥራል” ያለው አርቴታ “እስካሁን በህይወቴ ምርጥ ስሜት ከፈጠሩልኝ አጋጣሚዎች መካከል አንዱ ‘የሊጉ ሻምፒዮን’ የሚለው ድምጽ ነው” ሲል ተናግሯል።
የማንችስተር ሲቲን ወሳኝ ጨዋታ በቀጥታ እንዳልተከታተለ የገለጸው አርቴታ፣ በቤቱ ውስጥ የተፈጠረውን ያንን ታሪካዊና ልብ የሚነካ ቅጽበት ሲያስታውስ“ከውስጥ ድምጽ ሰማሁ፥ ልጄ በሩን ከፍቶ እየሮጠ ወደ እኔ መጣ። በእምባ እየታጠበ ‘አባዬ ሻምፒዮን ሆንን!’ ብሎ ነው ያበሰረኝ ሲል ገልጿል።
አሰልጣኙ አክሎም “ልጄ ነው እያለቀሰ የክብር ዜናውን ያበሰረኝ” ብሏል።
ይህንን ታላቅ ስኬት ለመጨበጥ ከተጓዘበት ረጅም እና ውጣ ውረድ የበዛበት መንገድ ምን እንደተማረ የተጠየቀው አርቴታ፣ ” ትሁት መሆን እና ለማወቅ መጓጓትን”ተምሬበታለሁ ሲል ተደምጧል።
እግር ኳስ ከሜዳው ታክቲክ እና ከ90 ደቂቃ ፍልሚያ በላይ የቤተሰብ፣ የፅናት እና የማይበገሩ ህልሞች ድምር ውጤት መሆኑን አርቴታ እና ልጁ በዚያች ምሽት አሳይተውናል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ
“የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መባል ስሜቱ የማይታመን ነው!”— ሚኬል አርቴታ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።