የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና አርባምንጭ ከተማን በመርታት ወደ አሸናፊነት ተመለሰ
በ33ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ መሪው ሲዳማ ቡና አርባምንጭ ከተማን 3ለ0 በመርታት ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ለሲዳማ ቡና የማሸነፊያ ጎሎችን መስፍን ታፈሰ ሁለት ኳሶችን ከመረብ ሲያሳርፍ ኢያሱ ቀሪዋን ጎል ታምራት በራሱ ላይ አስቆጥሯል።
በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመራው ሲዳማ ቡና ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት በመመለስ ከተከታዩ መቻል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 5 በማስፋት መሪነቱን አጠናክሯል።
አርባምንጭ ከተማ በበኩሉ በውድድር ዓመቱ 14ኛ ሽንፈቱን በማስተናገዱ በሊጉ ለመቆየት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና ነጥቡን 58 በማድረስ በፕሪሚዬር ሊጉን አናት ላይ ሲገኝ አርባምንጭ ከተማ በአንፃሩ በ29 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
በ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በንቃት በመሳተፍ የሚፈልገውን መንግስት ለመምረጥ መዘጋጀት እንዳለበት ተገለጸ
ክልሉን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው – አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል
የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ዞን አቀፍ ማጠቃለያ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እየተካሄደ ነው