በ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በንቃት በመሳተፍ የሚፈልገውን መንግስት ለመምረጥ መዘጋጀት እንዳለበት ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ግንቦት 24 በሚካሄደው 7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በንቃት በመሳተፍ የሚፈልገውን መንግስት ለመምረጥ መዘጋጀት እንዳለበት ተገልጿል፡፡
ሴንተር ፎር ኢምፓወርመንት ኢትዮጵያ የተሰኘ ሲቪክ ማህበር ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር በጎፋ ዞን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።
የሴንተር ፎር ኢምፓወርመንት ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር ብስራት ኤሊያስ በሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች በንቃት በመሳተፍ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ሊመጠቀሙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ምርጫው ሰላማዊ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት ያለው እንዲሆን የጸጥታ አካላት የሃይማኖት ተቋማት እና የሲቪክ ተቋማት ድርሻ የላቀ መሆኑን አንስተዋል።
የማህበሩ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ታደሰ እና የምርጫ ዘርፍ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ኤርሚያስ ጢላ ባለድርሻ አካላት በቂ ግንዛቤ አግኝተው መራጩ ሕዝብ ወቅቱን ጠብቀው በምርጫ ቀን የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ በዕውቀት ላይ ተመሥርተው ድምፅ እንዲሰጡ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ የስልጠና መድረክ ነው ብለዋል።
የጎፋ ምርጫ ክልል አንድ አስተባባሪ አቶ በላይ ባበና በምርጫ ክልሉ ባሉ 81 ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው የተሳካ እንዲሆን ህብረተሰቡ የፈለገውን የፖለቲካ ፓርቲ እንዲመርጥ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ያነጋገርናቸው የሰላምና ጸጥታ፣ የኮሙኒኬሽንና የፖሊስ አመራሮች በሰጡት አስተያየት ከስልጠናው በቂ ግንዛቤ በማግኘታቸው ዜጎች በምርጫው የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማድረግ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
ክልሉን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው – አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል
የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ዞን አቀፍ ማጠቃለያ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እየተካሄደ ነው
የብልጽግና ፓርቲ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን በመፍጠር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ የልማት ሥራዎችን እየተገበረ ይገኛል – አቶ አንተነህ ፈቃዱ