የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ዞን አቀፍ ማጠቃለያ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እየተካሄደ ነው
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ዞን አቀፍ ማጠቃለያ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የሸካ ዋና መቀመጫ በሆነችው ቴፒ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በነቂስ በመውጣት ለፓርቲው ያለቸውን ድጋፍ ገልፀዋል።
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያ በዲሞክራሲ ጎዳና የጀመረችውን ጉዞ የምታጸናበት ነው፣ በመደመር እሳቤ ወደ ብልጽግና፣ ብልጽግና ጉዞ በህዝብ ይሁንታ ይቀጥላል፣ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር፣ የሚሉትንና ሌሎች መፎክሮችን በሰልፉ ላይ ደጋፊዎች አሰምተዋል።
ዘጋቢ፡ ታሪኩ ታደሰ – ከሸካ ጣቢያችን
የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ዞን አቀፍ ማጠቃለያ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እየተካሄደ ነው

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው