የብልጽግና ፓርቲ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን በመፍጠር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ የልማት ሥራዎችን እየተገበረ ይገኛል – አቶ አንተነህ ፈቃዱ

የብልጽግና ፓርቲ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን በመፍጠር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ የልማት ሥራዎችን እየተገበረ ይገኛል – አቶ አንተነህ ፈቃዱ

ሀዋሳ፡ ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የብልጽግና ፓርቲ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን በመፍጠር የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ የልማት ሥራዎችን እየተገበረ እንደሚገኝ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ ገለፁ።

በከምባታ ዞን ዶዮገና ከተማ በከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ የታጀበ የብልጽግና ፓርቲ የይምረጡኝ ቅስቀሳ እና የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በድጋፍ ሰልፉ ወቅት የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ እንደገለፁት፤ የለውጡ መንግሥት ያስመዘገባቸው ሁለንተናዊ የልማት ስኬቶችና የህዝብ ተጠቃሚነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በትኩረት ይሰራል።

ይህ ታላቅ የህዝብ ንቅናቄ የለውጡ መንግሥት ላስመዘገባቸው ሁለንተናዊ የልማት ስኬቶችና የህዝብ ተጠቃሚነትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለብልፅግና ፓርቲ ይሁንታን የሚሰጥ መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል።

አቶ አንተነህ አክለውም፤ ፓርቲው ባለፉት 8 ዓመታት በመንገድ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በመስኖ እና በግብርና ዘርፎች በርካታ የልማት ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጸው፤ ይህ ለውጥ በሕዝብ እና በመንግሥት የጋራ ትብብር የተገኘ መሆኑን አስታውቀዋል።

ፓርቲው አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን በመፍጠር በርካታ የልማት ሥራዎችን እየተገበረ የሚገኝ መሆኑን በመጠቆም።

የብልግና ፓርቲ በአይን የሚታይ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣና ኢትዮጵያን ለማበልጸግ እየሠራ ያለ ትጉህ ፓርቲ መሆኑን በመጠቆም፤ የለውጡ መንግስት የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ደረጀ በደረጀ እየፈታ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ይበልጥ ለማሳደግ በሚያደርገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ በመጠቆም።

የከምባታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አረጋ እሸቱ በበኩላቸው፤ የብልጽግና ፓርቲ የመደመር ፍልስፍናን በተግባር ያሳየ እና ለዜጎች ተጠቃሚነት ልዩ ተኩረት ሰጥቶ እየሠራ የሚገኝ ፓርቲ ነው ብለዋል።

የዶዮገና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አየለ ጋርከቦ እንደገለፁት፤ የለውጡ መንግስት በሕብረተሰቡ ሲነሱ የነበሩ የመሠረተ ልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ባለፉት 8 ዓመታት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን አከናውኗል።

በድጋፍ ሰልፉና የይምረጡን ቅስቀሳ ወቅት የተገኙ የተለያዩ የህበረተሰብ ክፍሎች በበኩላቸው ፓርቲው ከፌዴራል ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ድርስ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሠረተ ልማቶችን በማከናወን ላይ የሚገኝ የህዝብ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የፖሊስ አባላትን እና ሌሎች አደረጃጀቶችን በመጠቀም እየተሰራ መሆኑን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ሙላቱ ተስፋዬ ገልጸዋል።

በድጋፍ ሰልፉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱን ጨምሮ የክልሉ ፕላን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጣው፣ የከምባታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አረጋ እሸቱ እና ሌሎች የየመዋቅሩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ: መልካሙ ታፈሰ – ከሆሳዕና ጣቢያችን