የጂንካ ከተማ አስተዳደር የኦንላይን ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በይፋ ስራ ጀመረ
ማዕከሉን በይፋ ስራ የያስጀመሩት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ ናቸው።
የክልሉ ዋና አፈ ጉባኤና የአመራር ቡድናቸው በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጡ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል ይሆኑ ዘንድ የተቋቋመውን የከተማ አስተዳደሩ የኦንላይን ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ጎብኝተዋል።
የተሳለጠ የኦንላይን የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ማቅረብ እንዲቻል የተጀመረው ማዕከሉ፤ በተገቢው መንገድ አገልግሎት ማቅረብ ሲችል የዜጎች እንግልትን የሚቀንስ በመሆኑ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ የኦንላይ አገልግሎት ለዜጎች መሰጠቱ ዜጎች ባሉበት ሆነው በእጅ ስልካቸው ብቻ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኝ የሚያስችል መሆኑን ነው የማዕከሉ አስተባባሪ አቶ ተመስገን ጋናቡል የገለጹት።
ለዚህ አገልግሎትም ከ1 ሺህ 5 መቶ በላይ ዜጎች ወደ ምዝገባ ስርዓት የገቡ ሲሆን ሌሎችም መጥተው አካውንት በመክፈት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ: ወንድሜነህ አድማሱ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው