ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በዳሞት ጋሌ ወረዳ የጫራቄ ወንዝ ላይ የተገነበውን ተንጠልጣይ ድልድይ መርቀው ከፍተዋል
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉ መንግስት በወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ በጫራቄ ወንዝ ላይ ያስገነባውን ተንጠልጣይ ድልድይ መርቀው ከፍተዋል።
በዳሞት ጋሌ ወረዳ ሀርቶ ቆንጦላ ቀበሌ የጫራቄ ተንጠልጣይ ድልድይ በክልሉ መንግስት የተገነባ ሲሆን ዳሞት ጋሌ ወረዳን ከድጉና ፋንጎ ወረዳ ጋር የሚያገናኝ 126 ሜትር ርዝመት ያለው ነው።
ድልድዩ ከ22 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን የድልድዩ መመረቅ ከዚህ ቀደም በህብረተሰቡ ላይ ይደርስ የነበረውን ጉዳት ያስቀረ እና በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች እንዳሉት ተገልጿል።
የዘመናት የህዝብ ጥያቄ የሆነው ይህ ድልድይ በግብርና ምርት እምቅ አቅም ያላቸውን ቀበሌዎች ከሌሎች አካባቢዎች ጋር በማስተሳሰር ረገድ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
ምንጭ፡ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው