የተፈጥሮ ማዳበሪያን በመጠቀም ከተሞችን ፅዱና ምቹ ከማድረግ ባሻገር የኤክስፖርት ምርትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ገለጸ
የግብርና ተረፈ ምርትን መልሶ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ስራ ከዩኒቨርሲቲው ጋር እየሰራ እንደሚገኝ የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ ።
”የኤስ ዲ ሲ”ፕሮጀክት በዘርፉ ከተማን ከገጠር የማስተሳሰር ስራ ከማከናወኑም ባሻገር የቴክኖሎጂ ሽግግር እያደረገ እንሚመገኝ ተጠቃሚዎች ተናገሩ።
መንግስት የአፈር ለምነትን ለማሳደግ፣ ቆሻሻ ዋጋ እንዲያገኝ ብሎም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት የተፈጥሮ ማዳበሪያ የመጠቀም ባህልን ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል ።
በሲውዘርላንድ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በ 4 የአፍሪካ ሀገራት በቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ላይ የሚሰራው “የኤስ ዲ ሲ” ፕሮጀክትም ይህንን ዕቅድ ለማሳካት በጋሞ ዞን እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ቴክኖሎጂው ምዕራብ አባያ ከተማ ይፋ ሲደረግ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የከተመ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አብረሀም አይካ በከተመው ቆሻሻን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ማስወገድ የሚያስችል ፕሮጀክት የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂውን ይፋ ማድረጉ የሚመሰገን መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ ምርትና ምርታማነት ከማሳደጉም ባሻገር የብርብር ከተማ የቆሻሻ ማስወገጃ ሥነ-ዘዴ እንዲዘምን አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።
በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዴንት ተክሉ ወጋዬሁ (ዶ/ር) ፤ ፕሮጀክቱ በከተማው አስፈላጊ ቆሻሻን ወደ ኮምፖስት ወይም “ቀርስ” እንዲቀየር ከመደገፍ ባሻገር ከተማን በማፅዳት የስራ እድል መፍጠር ላይ ትኩረት ማድረጉን ገልፀዋል ።
ከተማዋም ከፍተኛ ሙዝ አምራች ከመሆኗ ጋር ተደማምሮ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአከባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑንም ተክሉ ወጋዬሁ (ዶ/ር)፤ አብራተዋል።
ወ/ሮ ቪቪያን ኦሴሌ” የኤስ ዲ ሲ “ፕሮጀክት ተወካይ ሲሆኑ በአንድ አመት ውስጥ ኮምፖስት የመጠቀም ባህላችሁ ማደጉን ተመልክቻለሁ በቀጣይም በጋራ በመስራት በአከባቢው ብሎም በዞኑ ለውጥ ለማምጣት እንሰራለን ብለዋል።
የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ ተወካይና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ማጌሶ ማሾሌ ፤ የአርባምንጭ የኒቨርሲቲ በዞኑ በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን ገልፀው ቆሻሻን ወደ ጥቅም ለመቀየር እየተደረገ የሚገኘው ጥረት ቀጣይነት እንዲኖረው ዞኑ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
በዞኑ የግብርና ተረፈ ምርቶችን መልሶ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ህያው ለውጥ እያመጡ መሆኑን የተናገሩት አቶ ማጌሶ ዘርፉ ለበርካቶች የስራ ዕድልም መፍጠሩንም ጭምር ጠቁመዋል ።
የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎ በበኩላቸው ችፕሮጀክቱ ከተማን ከገጠር የሚያስተሳስር ፤ ትልቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ የቴክኖሎጂ ሽግግሩን ለማስፋት መሰራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።
በመጨረሻም የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አባይነህ ፈይሶ ስለ ፕሮጀክቱ ገለፃ የሰጡ ሲሆን የተፈጥሮ ማዳበሪያን የሚያመርት ዘመናዊ የትራክተር ቁልፍ ርክክብ ተከናውኗል ።
ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
የተፈጥሮ ማዳበሪያን በመጠቀም ከተሞችን ፅዱና ምቹ ከማድረግ ባሻገር የኤክስፖርት ምርትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ገለጸ

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)