ወጣቶች የፊታችን ግንቦት ወር በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የዲሞክራሲ ባህል ማሳደግ እንደሚገባቸው በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
የይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ክንፍ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች “ወጣት ይመርጣል ሀገር ይፀናል” በሚል መሪ ቃል የይምረጡ ቅስቀሳ በከተማው መርሐ-ግብር ተካሄል።
የከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ብዙአየሁ ታደሰ፤ ወጣቶች 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የዲሞክራሲ ባህል ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሁሉም ደረጃዎች ሰላማዊ፣ ፍትሀዊና በሕዝቡ ዘንድ ተአማኒነት ያለው እንዲሆን ወጣቱ የማይተካ ሚናውን መወጣት እንደሚገባው ከንቲባው አሳስበዋል።
ወጣቱ በምክንያታዊነት የሚያምንና በሀሳብ የበላይነት የሚሞግት መሆን እንዳለበት የጠቆሙት ከንቲባው፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በይርጋጨፌ ከተማ ከመዋቅር ለውጥ አንስቶ የበርካታ ለውጦች ተጠቃሚ መሆናቸውን አቶ ብዙአየሁ አብራርተዋል።
ፓርቲው የጀመረውን አሻጋሪ አመለካከት በማህበረሰቡ ውስጥ በማስረጽ ባለፉት ጥቂት አመታት በተከናወኑ ሥራዎች የላቀ ውጤት ተመዝግቧል ሲሉም ከንቲባው በንግግራቸው አመላክተዋል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ ኢንጂነር ተመስገን ጥላሁን በበኩላቸው፤ ብልፅግና ፓርቲ እንደ ሀገር ለሚወዳደርበት የስንዴ ነዶን የምርጫ ምልክት አድርጎ የመጣበት ዋነኛው ምክንያት የኢኮኖሚ ሉአላዊነት ለማመላከትና የመደመር እሳቤን በተግባር ለማረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል።
ከጋራ ትርክት ውጪ የሚንጸባረቁ ነጠላ ትርክቶችን በማስወገድ በህዝቦች መካከል አንድነት መፍጠር ተገቢ ስለመሆኑም ኃላፊው ጠቁመዋል።
ከመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች መካከል ወጣት መላኩ አፈወርቅና ዘካሪያስ ከበደ ለሀገር ግንባታ ሥራ ምርጫ ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ምርጫው ሠላማዊ እንዲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ወጣቶቹ እለቱን በማስመልከት በይርጋጨፌ ከተማ የእግር ጉዞ በማድረግ የይምረጡ ቅስቀሳ መርሐ-ግብሩ ተጠናቋል።
ዘጋቢ: ዘርሁን ሹፌር – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
ወጣቶች የፊታችን ግንቦት ወር በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የዲሞክራሲ ባህል ማሳደግ እንደሚገባቸው በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር ገለፀ

More Stories
የተፈጥሮ ማዳበሪያን በመጠቀም ከተሞችን ፅዱና ምቹ ከማድረግ ባሻገር የኤክስፖርት ምርትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ገለጸ
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለተመራቂ ተማሪዎቹ የተሻለ የስራ እድልና መነሳሳት ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገለፀ
ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በተገኙበት ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሠልፍ በታርጫ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል