ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በተገኙበት ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሠልፍ በታርጫ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል
ከየወረዳው የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሠልፉ ተሣትፈዋል።
በሠልፉ ላይ የፓርቲው የምርጫ ምልክት “የስንዴ ነዶ” ምስል አእንዲሁም የተለያዩ መፈክሮች እየተስተጋቡ ይገኛሉ።
የፈረስ ጉግስ፣ የባህላዊ መሣሪያዎች ጨዋታ፣ ስፖርት ትርዒት እና የመሳሰሉ ሁነቶችም የሰልፉ ድምቀት ሆነው ታይተዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ታርጫ ብዝሃ ከተማ እየተካሄደ ባለው የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ሠልፍ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ መካሻ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው