በተለያዩ መስኮች የተመዘገቡ ድሎችን ይበልጥ ለማሳደግ የህዝቡ ድጋፍ በምርጫ መረጋገጥ አለበት – ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

በተለያዩ መስኮች የተመዘገቡ ድሎችን ይበልጥ ለማሳደግ የህዝቡ ድጋፍ በምርጫ መረጋገጥ አለበት – ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

ሀዋሳ፡ ግንቦት 10/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በተለያዩ መስኮች የተመዘገቡ ድሎችን ይበልጥ ለማሳደግ የህዝቡ ድጋፍ በምርጫ መረጋገጥ እንደአለበት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ በተለያዩ ኩነቶች የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በሰልፉ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)
ብልጽግና ፓርቲ ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነት የጎደለባቸውን አካባቢዎች በትኩረት በመለየት የመሠረተ ልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቂዎችን እየፈታ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ብልጽግና በክልሉ ብሎም በዞኑ ያሉ እምቅ አቅሞች እንዲለሙና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በተጨማሪም በብልጽግና ፓርቲ በሀገሪቱ በተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በክልሉ ዘርፈ-ብዙ የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች መሰራታቸውን አስረድተዋል።

በክልሉ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማስቀጠል ብሎም ሌሎችንም ለመጀመር ህዝቡ ብልፅግና ፓርቲን ይምረጥ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን፤ ብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ህዝብ በራስ የመደራጀት ጥያቄን ከመመለስ ጀምሮ ሌሎች ሰፋፊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መመለሳቸውን ተናግረዋል።

ፓርቲው የህዝቡን ጥያቄ ደረጃ በደረጃ እየፈታ ሁሉ አቀፍ ዕድገት እንዲመዘገብ አድርጓል ያሉት አቶ ፍቅሬ፤ በቀጣይ የተጀመረውን ዕድገት በማስቀጠል በአፍሪካ ብሎም በዓለም ተምሳሌት ለማድረግ በሚሰራው ስራ ህዝቡ ብልፅግናን እንዲመርጥ ጥሪ አቅርበዋል።

የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ፤ ባለፉት የለውጥ አመታት የህብረተሰቡን ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ሥራዎች መሠራታቸውን ገልፀዋል።

በተለይም ብዝሃ-ዘርፍ ኢኮኖሚ አማራጮችን በመዘርጋት እንደኮንታ ዞን ያሉ አካባቢዎች እምቅ አቅማቸው ተለይቶ እንዲለሙ መደረጉን አስረድተዋል።

በዚህም በብልፅግና ፓርቲ መሪነት በዞኑ ዘርፈ-ብዙ ዕድገቶች መምጣታቸውን በመግለፅ በዞኑ የመጡ ልማቶችን ለማስቀጠል መራጩ ህዝብ ብልፅግና ፓርቲን እንዲመርጥ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመርሀ-ግብሩ የክልሉን ርዕሰ መስተዳደር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስትና የፓርቲ ሀላፊዎች፣ የዞንና የወረዳ ባለድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ ተገኝተዋል።

ዘገቢ፡ ደረጀ ተፈራ – ከዋካ ጣቢያችን