ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶ፣ የዕጩ ማስተዋወቂያ እንዲሁም የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ አካሄደ

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍፁም ሠላማዊ፣ ነፃና ዲሞክሲያዊ እንዲሆን የፓርቲው አባላት ሚና የጎላ መሆኑም ተገልጿል።

‎ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በጎፋ ምርጫ ክልል አንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ አቶ እንድሪያስ ኤሮ፤ ፓርቲው ህብረብሄራዊ አንድነትን በማጠናከር ህዝባዊ መሠረት ላይ ያተኮረ ለሁሉም ምቹ የሆነች ሀገር ለመፍጠር በትኩረት የሚሰራ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአገሪቱ ህብረብሄራዊ አንድነትን ለመፍጠርና ወጣቱን በልማቱ የነቃ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ ፓርቲው ይሰራል ብለዋል።

‎ኀብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሲሳተፍ በሀገር ደረጃ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ አንስተው፤ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፍትሐዊ እንዲሆን የበኩላቸውን እንዲወጡ ለአባላቱና ደጋፊዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

‎የህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አበራ በቀለ፤

‎ፓርቲው የህብረብሄራዊ አንድነትን በማጠናከር ህዝባዊ መሠረት ያለን፣ በርካታ መሰናክሎች አሸንፈን የሁሉም የሆነች ሀገር ለመፍጠር በሀሳብ የበላይነት የሚወዳደር ፓርቲ በመሆኑ ህብረብሄራዊ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የምርጫ ምልክታችንን የአደይ አባባ በመምረጥ ለፓርቲው ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

‎የህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ዋና ፀሐፊና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታምራት አሰፋ፤ ሰላማዊ ትግል በማድርግ

በሀገር ደረጃ ለውጥ ለማምጣት ኀብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲን እንዲመርጡ ጥሪ አቀርበዋል።

‎የፓርቲው አባላት የእግር ጉዞ በማድረግ የምርጫ ቅስቀሳቸውን አጠናቀዋል።

‎ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን