የ3ኛው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር አማሮ ኬሌ ክለብ ሻምፒዮን ሆነ
የደረጃ ጨዋታውን ምዕራብ አባያ ከገሱባ አቻው አድርጎ ምዕራብ ከባያ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
አርባምንጭ ዙሪያ ከነማ ከኬሌ ከነማ አቻው 3ኛውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ፍፃሜ ውድድር የተገናኙ ሲሆን በሙሉ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት አጠናቀው በተሰጣቸው መለያ ምት አማሮ ኬሌ አርባምንጭ ዙሪያን 5ለ4 በሆነ ውጤት በማሸነፊ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ወ/ሚካኤል መስቀሌ አጠቃላይ ውድድሩ ስኬታማ እንደነበር ገልፀዋል።
ውድድሩን ለ3ኛ ጊዜ የኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ በማዘጋጀት ሀላፊነቱን መወጣቱን የጠቀሱት ሀላፊው፤ ለውድድሩ ስኬት ለተረባረቡ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ኦላዶ ኦሎ፤ በውድድሩ ብቁ ስፖርተኞችኝ መመልከት የተቻለበት እንደሆነ ገልፀዋል።
አጠቃላይ ውድድሩ ያለምንም ችግር መጠናቀቁን ሀላፊው ጠቅሰው በመላው ኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና አምስት ክለቦችን እንደሚያሳትፍ ተናግረዋል።
ለውድድሩ ድምቀትና ስኬት ለተረባረቡ ሁሉ አቶ ኦላዶ ምስጋና አቅርበዋል።
የኣሪ ዞን ባህልና ስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊና የዕለቱ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ ሲሳይ ጋልሺ፤ ለውድድሩ ስኬት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በዚህ ልክ ያለ ምንም ችግር ተጠናቋል ብለዋል።
ለ3ኛ ጊዜ ዞኑ ዕድል አግኝቶ ውድድሩን እንዲያስተናግድ በመደረጉ ክልሉን አመስግነው፤ መላው የጂንካ ከተማና በዙሪያ ያሉ ማህብረሰብ እንግዶችኝ ተቀብለው ላደረጉት ትብብርና አገልግሎት በዞኑ እስተዳደር ስም አመሰግነዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ደመላሽ ይትባረክ በበኩላቸው፤ ውድድሩ ለሀገር አቀፍ ሊሆኑ የሚችሉ ስፖርተኞች የታዩበት ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ለ3ኛ ዙር ዕድሉን አግኝቶ አዘጋጅ የሆነው የጂንካ ከተማ በብቃት ውድድሩን ማስተናገዱን አቶ ደመላሽ ተናግረው ለዚህም አመስግነዋል።
አጠቃላይ ተጫዋቾችና ከሰልጣኞች የነበራቸው ቆይታ ስኬታ ነበር ሲሉ ገልፀው የጂንካ መወዳደሪያ ሜዳ በወቅቱ የአር ፀባይ ተጫዎቾች በአግባቡ እንዳይጫወቱ አሉታዊ ተጽዕኖ መፍጠሩን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በመላው ኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና ኬሌ ከነማ፣ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ከነማ፣ ምዕራብ ዓባያ ከነማ፣ ገሱባ ቀጥታ ተሳታፊ መሆናቸውን ሲያረጋግጡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተጨማሪ አንድ ክለብ እድል በመስጠቱ ከተሳተፉ ለክልሉ ውጤት ሊያስገኝ የሚችል አንድ ምርጥ ክለብ አምስተኛ ሆኖ እንደሚሳተፍ ተገልጿል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር የምርጥ ዘር ብዜት ስራን በራስ አቅም ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምርጥ ዘር ድርጅት አስታወቀ
በበልግ አዝመራ ከሚከናወኑ የግብርና ስራዎች ከ70 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዷል – አቶ ማስረሻ በላቸው
የመንግሥትን የልማት ክፍተቶችን ለመሙላት የሚሰሩ የማህበረሰብ ልማት ድርጅቶች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በተሻለ ለማረጋገጥ በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል – አምባሳደር ፍጹም አረጋ