7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ያነጋገርናቸው አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናገሩ
ግንቦት 24/2018 ለሚካሄደው ምርጫ ካርዳቸውን በመያዝ እየጠበቁ እንደሚገኙ አስተያየት ሰጪዎቹ አመላክተዋል።
በሆሳዕና ከተማ ካነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች መካከል ዳኛ ዘውዴ ሠላሙ፣ አቶ አትንኩት አሰፋ፣ አባይነህ ጳውሎስና ሲስተር በላይነሽ አንፎጬ እንደገለፁት፤ በቅድመ ምርጫ፣ የምርጫ ጊዜና ድህረ ምርጫ፥ ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ ህዝባዊ ቅቡልነት ያለውን መንግስት በመመስረት እንዲጠናቀቅ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል።
አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም፤ ሰፊውን የህብረተሰብ ክፍል ያቀፈው ወጣቱ እውቀቱን ለመልካም ዓላማ በመጠቀም ለሁሉ ዐቀፍ ሠላም የዜግነት ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
ምርጫ ሀገር የማስቀጠያ ሂደት መሆኑን በመጠቆም ሠላም ለሁሉ ዐቀፍ ሀገራዊ ልማት መሠረት መሆኑን በመገንዘብ እኛም የዜግነት ግዴታችንን ለመወጣት የድርሻችንን ኃላፊነት እንወጣለን ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በመጪው ግንቦት 24/2018 ለሚፈፀመው ጠቅላላ ምርጫ በካርዳቸው ይሆነኛል ያሉትን ፓርቲ በመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም ዝግጁ መሆናቸውንም አስተያየት ሰጪዎቹ ገልፀዋል።
ዘጋቢ: አማኑኤል አጤቦ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)