በኣሪ ዞን ሰሜን አሪ ወረዳ የራጺ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነች

በኣሪ ዞን ሰሜን አሪ ወረዳ የራጺ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነች

ከተማዋን ከቀበሌ የሚያገናኝ የ10 ኪሎ ሜትር የገጠር መንገድም በይፋ ተመርቋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ የተመራው የአመራሮች ቡድን በኣሪ ዞን የሰሜን አሪ ወረዳ የጀመረው የስራ ጉብኝት እንደቀጠለ ይገኛል።

በሁለተኛው ቀን የስራ ጉብኝታቸው ዋና አፈ ጉባኤው አቶ አለማየሁ ባዲ ከመሩት የአመራር ቡድን ጋር የተገኙት በዞኑ ሰሜን አሪ ወረዳ አርፋሮ ክላስተር በራጺ ታዳጊ ማዘጋጃ ከተማ ነው።

በከተማው የዘመናት የህዝብ ጥያቄ ምንጭ የነበሩ የመንገድና የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመመረቅ በይፋ አስጀምረዋል።

በዚህም ከተማዋ የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ መብራት አገልግሎት ተጠቀሚ መሆኗ በይፋ የተረጋገጠ ሲሆን በተመሳሳይ በአርፋሮ አካባቢ የሚገኘው የባዘራ – ራፂ 10 ኪሎ ሜትር መንገድንም መርቀው ከፍተዋል።

የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የወረዳው የአካባቢው ነዋሪዎች በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ደስታቸውን ሲገልጹ ተስተውለዋል።

ነዋሪዎቹም የዘመናት ጥያቄያቸው መልስ ያገኘበት ታሪካዊ ዕለት በመሆኑ መደሰታቸውን ተናግረዋል።

ዘጋቢ: ወንድሜነህ አድማሱ – ከጂንካ ጣቢያችን