በጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ

በጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂር ዳግማዊ አየለ፤ የብልፅግና ፓርቲ ለህዝቡ የሚያስፈልገውን መሠረታዊ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የገባውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

‎በቀጣይም በአካባቢው የተጀመሩ ሌሎች መሠረተ ልማቶች በጥራት እና በፍጥነት እንዲጠናቀቁ የዞኑ አስተዳደር ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

‎የዛላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንበስ ሀናና በበኩላቸው፤ ብልፅግና ፓርቲ ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት እንደ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌያት የሚሰሩ ልማቶች በጥራት ተሰርተው እንዲጠናቀቁ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

‎የሳልቤ እና የሻቺ ቀበሌያት ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ንጹህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩና የጠጠር መንገድ ከፈታ እየተደረገ መሆኑ የለውጡ መንግስት ትሩፋት መሆኑን ተናግረዋል።

‎አሰታየየታቸውን የሰጡን የአካባቢው ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውሃና የመንገድ መሠረተ ልማት የመልካም አሰተዳደር ጥያቄ ሆኖ ለረዥም ጊዜ መቆየቱን አስታውሰው፤ አሁን በተመረቀው የንጹህ መጠጥ ውሃና በመንገድ ከፈታ መደሰታቸውን ተናግረዋል።

‎በዕለቱ በዛላ ወረዳ በገልጣ ማልዓንተ፣ ገልጣ ዙሪያ፣ ሳልቤ እና ሻቺ ቀበሌያት የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ማስተዋወቂያ እና ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።

‎በመረሃ ግብሩ የዛላ ዳራማሎ ምርጫ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪና የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉነሽ ጉሌ ከፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች ጋር ትውውቅ አድርገዋል።

‎ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን