በሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ከ5 ሺህ 9 መቶ በላይ ተማሪዎች ክልላዊና ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸው ተገለፀ

በሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ከ5 ሺህ 9 መቶ በላይ ተማሪዎች ክልላዊና ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸው ተገለፀ

በወረዳው በሌሳ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያገኘናቸው ተማሪዎች በብሔራዊና ክልላዊ ፈተና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለተማሪዎች ውጤት መዳከም መንስኤ የሆኑ ችግሮችን በመለየት ለውጥ ለመምጣት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ መቆየቱን በዞኑ የሌሞ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የፈተና ዝግጅት አስተዳደርና የትምህርት ምዘና ቡድን መሪ አቶ ብርሃኑ ላዕመንጎ ገልጸዋል።

በወረዳው 5 ሺህ 9 መቶ 99 ተማሪዎች በስድስተኛ፣ በስምንተኛና አስራ ሁለተኛ ክፍል በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጡ የትምህርት መመዘኛ ፈተና እንደሚወዱ አቶ ብርሃኑ ጠቁመዋል።

ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በትምህርት ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዛሮች ከሚደረገው ክትትልና ድጋፍ በሻገር ለ62 ተማሪዎች በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት እየተሰጣቸው መሆኑንም አቶ ብርሃኑ አመልክተዋል።

የበሌሳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ፀደቀ ኤርስንቆ በትምህርት ቤታቸው 56 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የቤተ መጽሐፍትና የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን የማሟላት እንዲሁም የመምህራንና መንግሥታዊ የልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ ብርቱ እንደሆነም ርዕሰ መምህሩ አስረድተዋል።

በትምህርት ቤቱ 1 መቶ 13 ተማሪዎች የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እንደሚወስዱ የጠቆሙት ደግሞ የበሌሳ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ አማኑኤል ሾቢሶ ናቸው።

በበሌሳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑት የምስራች መላኩ እና ይድነቃቸው ያዕቆብ እንዲሁም ከበሌሳ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ተማሪ በረከት አያኖና ሌሎችም በሰጡት አስተያየት በመምህራን በኩል ከሚደረግላቸው ድጋፍ በሻገር አጋዥ መጽሐፍትን በማጥናት እና የተለያዩ ጥያቄዎችን በመስራት በክልልም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰጠው ፈተና ራሳቸውን እያዘጋጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዘጋቢ: መንግሥቱ ፊጣሞ – ከሆሳዕና ጣቢያችን