”ከተረጅነት ወደ ምርታማነት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው
በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቴ አለነ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር)፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) እና የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ተገኝተዋል።
በተጨማሪም በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎችና የግብርና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩም ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሉዓላዊነትና ክብር የሚል የመነሻ ሃሳቦች በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) የቀረበ ሲሆን በቀረው ጽሑፍ ላይም ውይይት በመደረግ ላይ ይገኛል።
ኢትዮጵያ በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በመኸርና በበልግ ወራት የሰብል ምርታማነት፣ በሌማት ትሩፋት እና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የሚያስችል እመርታዊ ውጤት በማስመዝገብ ላይ እንደምትገኛ መውይይቱ የተሳተፉ አካላት ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የዘመናት ተረጅነትን በማስቀረት ከራስ አልፎ ስንዴን ወደ ውጪ በመላክ ወደተሟላ ሀገራዊ ክብር መሸጋገር የሚያስችል የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንደምትገኛ በመድረኩ ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የግብርና ሚኒስቴር በትብብር የውይይት መድረኩንም አዘጋጅተውታል።
ዘጋቢ፡ ፋሲል ሀይሉ
”ከተረጅነት ወደ ምርታማነት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)