ሀገራዊ ለውጡ ዕውን የሆነበት 8ኛ ዓመት እና የብልጽግና ፓርቲ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ እንዲሁም የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ምረቃ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ቂልጦ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል
በፕሮግራሙ በወረዳው ቂልጦ ከተማ የተገነቡ ከ41 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ይመረቃሉ።
በህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር)፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የክልልና የዞን የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የብልጽግና ፓርቲ የአካባቢው ዕጩዎችና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል በመላው ሀገሪቱ እየተካሄደ የሚገኘው የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ፤ ብልጽግናን እመርጣለሁ፤ አሻራዬን አኖራለሁ፣ ከብልጽግና ጋር መጪው ጊዜ የከፍታ ነው፣ ብልጽግናን መምረጥ የኢትዮጵያን ከፍታ ማረጋገጥ ነው የሚሉና ሌሌች መፈክሮች ተስተጋብተዋል።
ዘጋቢ: ሙጂብ ጁሃር – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)