የህዝቡን የመንገድ መሠረተ ልማት ጥያቄ ለመፍታት በዕቅድ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ

የህዝቡን የመንገድ መሠረተ ልማት ጥያቄ ለመፍታት በዕቅድ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ግንቦት 02/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለመሸጋገር በሚናደርገው ጥረት በክልል ሆነ እንደ ሀገር የህዝቡን የመንገድ መሠረተ ልማት ጥያቄ ለመፍታት በዕቅድ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪና የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳንሳ ገለፁ።

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር በደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ ወረዳ በ2018 በጀት ዓመት ቦሽኮሮ-ሌሞ- በዞ (ኬንቾ) 26.37 ኪሎ ሜትር አዲስ የመንገድ ግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሂዷል።

‎ፕሮግራሙ በአባቶች ምርቃትና መልካም የሥራና የፍፃሜ ጊዜ እንዲሆን በመመኘት መርቀው ከፍተዋል።

‎የማሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልጋጋ ባሌንሳ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ በፖለቲካዊ ዘርፎች በርካታ ለውጦችን ያሰመበገበ መሆኑን ገልፀው፥ በቆዳ ሰፋት 205 ሺህ ሄክታር የሚሸፍንና 70 ሺህ ደንና 40 ሺህ ሊታረስ የሚችል መሬትን ጨምሮ በርካታ ሀብቶች ያሉበት ወረዳ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

‎አክለውም የአከባቢው አርሶና አርብቶ አደር ለቴክኖሎጂ ፈጣን እንደመሆኑ የደም ስር የሆነው የመንገድ መሠረተ ልማት የዘመናት ግንባር ቀደም ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ በመደረጉ ምስጋና አቅርበዋል።

‎የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ በንግግራቸው የዛሬዋን ቀን ለማየት በርካታ ውጣ ወረዶችን ማሳለፋቸው ገልፀው፥ ለዚህ በመብቃቱ ደስታቸው ወደር እንደሌለው ገልፀዋል።

‎የህዝቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄና ወረዳው በመንገድ መሠረተ ልማት ወደ ኃላ የቀረ ነገር ግን ብዙ ፀጋዎች ያላት ዕድሜ ጠገብ ወረዳ ናት ያሉት አቶ ማዕከል እንዳስጀመርነው ሁሉ ትልቁ ደስታ ስናሰመርቅ ነው ብለዋል።

‎የመንገድ የልማቱ የፖለቲካ ክፍፍል ሲፈጥር እንደነበር ያስታወሱት የዞኑ አሰተዳዳሪ፥ ኮንትራክተሮችም ሀገር እንደሚገነባ በማስብ የበኩላቸውን እንዲወጡና ህዝቡም የበኩሉን አሰተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልዴ ተስፋዬ የገጠር ትስስርን ለማረጋገጥ የመንገድ መሠረተ ልማት ቀዳሚውን ድርሻ እንደሚወስድ በማመን 30 በመቶ የኢትዮጵያ መንግስት ቀሪው 70 በመቶ በአለም ባንክ ድጋፍ ተሸፍኖ የሚስራ ይሆናል ብለዋል።

‎በዚህም በክልላችን በመንግስትና በአለም ባንክ በ8 ዞንና በ9 ወረዳ የመንገድ መሠረተ ልማቱ የሚሰራ ሲሆን ከዚህም አንዱ ይህ የምናስጀምረው ነው ብለዋል።

‎ለዚህም የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታ 154 ሚሊየን ብር በላይ በጀት ተመድቦ በ4 ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለማሰረከብ የሚስራ ሲሆን በግንባታውም ተንጠልጣይ ድልድዪችን ጨምሮ አድስ መንገድ ግንባታ ነባር ፣መንገድ ጥገና፣ ልዮ መሻገርያ ግንባታን ያካተተ ነው ብለዋል።

‎በክልላችንም በዚህ ዓመት 14 አዲሰ መንገድ 13 ነባር መንገድ ጥገናና ሌሎች ሥራዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 27 ኘሮጀክቶችን የውል ሰምምነት መፈፀማቸውን የቢሮ ኃላፊው ገልፀዋል።

‎ይህም የመንገድ ልማት ሥራ የዛሬው ጨምሮ 1.2 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚፈጅ ተናግረዋል።

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ረዳት የመንግስት ተጠሪና የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳንሳ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለመሸጋገር ለሚናደርገው ጥረት በክልላችን የህዝቡን የመንገድ መሠረተ ልማት ጥያቄ ለመፍታት በዕቅድ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ይህም ማሳያ መሆኑን አመላክተዋል።

‎ለዚህ ግንባታ ስኬታማ ሁሉም አርሶ አርብቶ አደር ተባባሪ እንድሆን አቶ ንጋቱ አሳስበዋል።

‎አሰተያየታቸውን የሰጡ የአከባቢው ነዋሪዎችም በግንባታው መጀመር መደሰታቸውን ገልፀው አሰፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።


‎ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን