በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ከነዋሪው ቁጥር ጋር የተመጣጠነ ትራንስፎርመር ባለመኖሩ ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮችና ለስጋት ተጋልጠናል ሲሉ አንዳንድ የቦቢቾ ቀበሌ ነዋሪዎች ተናገሩ
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሪጂን ሆሳዕና ቅርንጫፍ ጉዳዩን በዘላቂነት ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
በከተማው በቦብቾ ቀበሌ ከነዋሪው ቁጥር ጋር የተመጣጠነ ትራንስፎርመር እንዲቀርብ ለአመታት ሲጠይቁ መቆየታቸውን የገለፁልን አንዳንድ የቀበሌው ነዋሪዎች፤ በዚህም የኤሌክትሪክ አደጋ ስጋት እንዳለባቸው ገለፀዋል።
ከአመታት በፊትም በሰውና በቤት ላይ አደጋ እንደደረሰ አስታውሰው፤ አሁንም አደጋው እየተደጋገመ መሆኑን አብራርተዋል።
በቀበሌው ሰፊ ቁጥር ያለው ማህበረሰብ የሚኖር በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላaት ችግሩን አፅንኦት ሰጥተው እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
በከተማው በተለይም በቦቢቾ ቀበሌ የኤሌክትሪክ መቆራረጥና አልፎ አልፎ አደጋ እንደሚከሰት የገለጹት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሪጂን የሆሳዕና ቅርንጫፍ ዳይሬክተር አቶ አበበ ዕድሉ፤ የዚህ መነሻ የማህበረሰቡ የሃይል ፍላጎት ከሀይል አቅርቦት ጋር አለመመጣጠን መሆኑን አብራርተዋል።
ጉዳዩን በዘላቂነት ለመፍታት አካባቢውን ያማከለ የትራንስፎርመር ለውጥ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ዘላቂ መፍትሔ ላይ ለመድረስ እና ከአደጋውም ለመከላከል የአካባቢው ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ እቃዎች ስርቆት እንዳይኖር መጠበቅና ክትትል ማድረግ እንዲሁም አደጋ ሲኖር በፍጥነት ጥቆማ እንዲያደርሱ አሳስበዋል።
ዘጋቢ: ሳምራዊት ያዕቆብ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)