ብልፅግና ፓርቲ በየደረጃው የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት ያረጋገጡ በርካታ የልማት ተግባራትን ማከናውን መቻሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ የማታለም ቸኮል ገለጹ
በዳውሮ ዞን ቶጫ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የምርጫ ቅስቀሳ ሠልፍ ተካሂዷል።
በሠልፉ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ የማታለም ቸኮል፤ ብልፅግና ፓርቲ በየደረጃው የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት ያረጋገጡ በርካታ የልማት ተግባራትን ማከናውን መቻሉን ገልፀዋል።
አክለውም በሀገሪቱና በአካባቢያችን ያሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ብልፅግና ፓርቲን በመምረጥ ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ እንደሆነም ተናግረዋል።
የዳውሮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መላኩ ተረፈ በበኩላቸው፤ በብልጽግና ፓርቲ በርካታ የመዋቅር ጥያቄዎች የተመለሱ መሆኑን በመጠቆም በክልል የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ የህዝብ የልማት ጥያቄ እየተፈታ መምጣቱን አንስተዋል።
የማህበረሰቡ የጀግንነት መገለጫ የሆነው ሀላላ ኬላ ሪዞርት ተገንብቶ አገልግሎት መስጠቱም የብልፅግና ፓርቲ ትሩፋት ነው ብለዋል።
የዳውሮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ አስፋው ደሳለኝ፤ በአካባቢው በቃል ብቻ የሚነገርና ህልም የሆነውን የልማት ጥያቄ በፍሬና በተግባር ያሳየው የብልጽግና ፓርቲ መሆኑን አንስተው፤ አባላትና ደጋፊዎች ለፓርቲው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የቶጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምራት ታደሰ እንደገለፁት፤ የለውጡ መንግስት በሀገራችን የነበረውን ማህበራዊ፣ ኢኮሚያዊና ፖሊቲካዊ ችግሮችን በመቅረፍ ኢትዮጵያን ለሁሉም ዜጎች ምቹ እንድትሆን አስችሏል።
በወረዳውም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ፣ የመስኖ ልማት፣ የመንገድ ድልድይና መሠል የልማት ፕሮጀክቶችን በማውረድ ማህበረሰቡ ተጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል።
በወረዳው በተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ ድጋፍ ሠልፍ ላይ በርካታ ከቀበሌያት የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮችና የፓርቲው ዕጩዎች ተገኝቷል።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ መካሻ – ከዋካ ቅርንጫፍ

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)