ብልጽግና ፓርቲ በሀገሪቱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እየፈታ መምጣቱ ተገለፀ
በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ የብልጽግና አባላትና ደጋፊዎች የይምረጡኝ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል ።
በሰልፉ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፀሐይ ደርጫ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡
ፓርቲው በሀገሪቱ እና በአካባቢያችን የልማት ትሩፋቶችን ከማረጋገጥ አኳያ በሁሉም ዘርፍ በርካታ ስራዎችን እየሠራ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ፤ ብልጽግና ፓርቲ የህዝቦች ጥያቄዎች የሆኑትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ እየመለስ የመጣ ፓርቲ መሆኑም ገልጸዋል።
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲን በመምረጥ የተጀመሩ የስኬት ጉዞዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በበኩላቸው፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከተስፋ ወደ ብርሃን የመሸጋገር ዘመን መሆኑን በመጠቆም በአካባቢያችንና በሀገሪቱ የተሠሩ የልማት ተግባራትን ለአብነት የህዳሴ ግድብ፣ የሀላላ ሎጅ፣ ዳና ሎጅ፣ ገበታ ለሀገር፣ ገበታ ለሸገርና ሌሎችም የተለያዩ ግዙፍ
ፕሮጀክቶች መመረቅ የብልጽግና ውጤት እንደሆነም አስረድተዋል።
አክለውም ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በተጨማሪም ብልጽግና ፓርቲ በአብላጫ ድምጽ እንዲያሸንፍ የሰንዴ ነዶ የሆነውን ምልክት ላይ ድምጻቸውን እንዲሰጡ አቶ ዳዊት ለብልጽግና አባላትና ደጋፊዎች አሳስበዋል።
የማሪ መንሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳመነ ዳዋና፤ ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለዜጎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥና በሁሉም ዘርፍ ብልጽግና እንዲረጋገጥ እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ በፊት በአካባቢያቸው የመልካም አስተዳደር ችግር የሆነው የመዋቅር አደረጃጃት ምላሽ ያገኘው በብልጽግና መሆኑን በመጥቀስ፤ የተጀመሩ ልማቶችን ለማስቀጠል ብልጽግና ምርጫ እንዲሆን አሳስበዋል።
በድጋፍ ሰልፉ የተገኙት በርካታ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች እንደገለፁት፤ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሀገሪቱ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡
በድጋፍ ሰልፉ የምረጡኝ ቅስቀሳና የብልጽግና ፓርቲን በየደረጃው የሚወክሉ የእጩዎች ትውውቅ በማድረግ ሰልፉ ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ አሸናፈ ግዛው – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል