ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሴቶች ዘርፍ የልማት ህብረትና አደረጃጀት ማጠናከሪያ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሴቶች ዘርፍ የልማት ህብረትና አደረጃጀት ማጠናከሪያ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ራሔል ሌዊ

ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ በሁሉም ዘርፎች የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጋራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሀገር እድገት እንዲረጋገጥ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ወሳኝነት እንዳለው አብራርተው፤ ይህን ለማሣካት የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ ደግሞ የአደረጃጀቶች መጠናከር አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።

የሴቶች አደረጃጀቶችን ለማጠናከር እየተሰሩ የሚገኙ ተግባራትን አንስተው፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከ20 ሺህ በላይ የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀቶች እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በእነዚህ የልማት ህብረት አደረጃጀቶች ስር የሚገኙ አባላት ቁጥር ከ610 ሺህ ላይ መሆኑን ወይዘሮ ራሄል አስታውቀዋል።

የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሁሉም መዋቅር ዓላማ መሆኑን አመላክተው፤ ልማታዊ አመለካከትን ለመፍጠርና አደረጃጀቶችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ፣ የትምህርት ተሳትፎን ለማሣደግ፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶትን ለማስቀረትና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማጎልበት የልማት ህብረት አደረጃጀት አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በተለያዩ መዋቅሮች የሚገኙ የልማት ህብረት አደረጃጀቶችን በሚመለከት ግንዛቤ ለመፍጠርና በመጪው ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች በንቃት እንዲሳተፉ ማስቻልን ዓላማ በማድረግ መድረኩ መዘጋጀቱን አመላክተዋል።

በመድረኩ የሴቶችን አደረጃጀቶች ለማጠናከር የተከናወኑ ተግባራትን የሚያመላክት ሰነድ በቢሮው የልማት ህብረት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዘነበች ኃይለሚካኤል እየቀረበ ሲሆን፤ ውይይት እንደሚደረግበትም ይጠበቃል።

በመድረኩ የዞን እና የክልል የሴቶች አደረጃጀት አመራሮችና የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፉ ነው።

ዘጋቢ፡ ዮሐንስ ክፍሌ – ከቦንጋ ጣቢያችን