በአየር ንበረት ለውጥ እና በዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ ዘርፎች ዙሪያ የሚሠራው Vita/RTI-Ethiopia የተሠኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት በጎፋ ዞን የሥራ ማስጀመሪያ የትውውቅ መድረክ ተካሂዷል።
ላለፉት 22 አመታት በጋሞ ዞን አርሷደሩን ህይወት ለማሻሻል የሚረዱ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየው “Vit” ግበረ ሰናይ ድርጅት በቅርቡ የመንግስትን የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም በመደገፍ ደንን እንዳይወድም ማስቆምና ማልማት ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ የVita – RTI Ethiopia ፕሮጀክት ሳውላ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ለማ ወንድሙ ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ በጎፋ ዞን በሚኖረው ቆይታ የእናቶች ኩሽና ከሶስት ጉልቻ ይልቅ በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ከማድረግ አኳያ የሚሠሩ ተግባራት መኖራቸውን አቶ ለማ አብራርተዋል።
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በዞኑ በተፈጥሮና አካባቢ ጥበቃ ላይ ከሚሠሩ ፕሮጀክቶች “Vita” ሁለተኛው መሆኑን አስታውሰው የአካባቢው ማህበረሰብ ለመልማት ካለው ፍላጎት አኳያ በጋራ ለመሥራት ቁርኛ ነው ብለዋል።
ጎፋ ዞን ካለው የመሬት አቀማመጥና አየር ንብረት አኳያ ሰፋፊ ተግባራትን ማከናወን የማያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን የገለጹት አስተዳዳሪው ፕሮጀክቱ ወደ ዞኑ እንዲመጣ ላደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በዕለቱ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች የፕሮጀክቱ ሠራተኞች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ፕሮጀክቱ ስለሚያከናውናቸው ተግባራትና በሚካተቱ አካባቢዎች ዙሪያ ገለጻ ተደርጎ ውይይት ተካሂዷል።
በቀረበው ዕቅድ ላይም ተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየታቸውን አክለዋል፤በተለይም ፕሮጀክቱ የያዘው ዕቅድ ተገቢውን ድጋፍ ካገኘ በአጭር ግዜ ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል አረጋግጠዋል።
ለሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከሰጠው ትኩረት አኳያ የተፈጠረውን ዕድል ተጠቅሞ የዞኑ እናቶች እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በዞኑ ከፍተኛ አመራሮችና በአስተባባሪዎች በተሰጠው ማብራሪያ እንደተመላከተው” Vita”በበጀት የሚወሰን ሳይሆን እንየ አስፈላጊነቱና ቅድሚያ በሚሰጠው ጉዳይ ላይ ያለ ገደብ የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል