በድጋፍ ሰልፉ ከማሻ ከተማና ማሻ ወረዳ የተውጣጡ የፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ፤ ፓርቲው በሀገር ደረጃ ታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ብቻ ሳይሆን የባህር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።
የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት እንዲሁም የሀገር በቀል እውቀቶች እንዲጠናከሩ የብልፅግና ፓርቲ በሰራው ጠንካራ ስራ ውጤታማ ለውጥ እያስመዘገበ ይገኛል ያሉት አቶ አበበ፤ የዞኑን ሰላም የመለሰ፣ የመብራት፣ የሆስፒታል ተጠቃሚነትን እና የህዝቡን ሁለንተናዊ እድገት እያረጋገጠ የሚገኝ ፓርቲ ነው ብለዋል።
የዲሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አዝመራ አንደሞ፤ የብልጽግና ፓርቲ ላለፉት 25 አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ እዳ እያረመና እየከፈለ ምንዳ እያሰፋ ውጤታማ ለውጥ በሀገሪቱ እያስመዘገበ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑን ለሰልፉ ታዳሚዎች ጠቁመዋል።
ብልፅግና ሰው ተኮር የሆነና አካታች የፖለቲካ ተሳትፎ እያረጋገጠ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑን የገለፁት አቶ አዝመራ፤ ጠንካራ ተቋሟትን እየገነባ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ለውጥ በማረጋገጥ ላይ እየሰራ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑን ተናግረዋል።
በማህበራዊ ልማት እየሰራ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑን የገለፁት አቶ አዝመራ፤ የኢትዮጵያን ቀጣይነት ማረጋገጥ፣ የፈረሱ ቤቶችን መገንባት፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ላይ ፓርቲው በቆራጥነት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ተወካዮችን መምረጥ ብልፅግናን ማስቀጠል እና የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ በመሆኑ ድምፃቸውን ሳያባክኑ በመስጠት ድጋፋቸውን እንዲያረጋግጡ ለሰልፉ ታዳሚዎች ገልጸዋል።
የሰልፉ ታዳሚዎች በበኩላቸው፤ የብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አምስት አመታት የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች እንዲሁም በዲፕሎማሲ ውጤታማ ለውጥ ማስመዝገብ ችሏል ብለዋል።
ከታዩ ለውጦች መካከል ለዘመናት የህዝብ ጥያቄ የነበረውን በክልል የመደራጀት መብት ከማረጋገጥ በተጨማሪ በተለያዩ መሰረተ ልማቶች የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ አንዱ የፓርቲ ውጤት ነው ሲሉ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል የማሻ ከተማና ማሻ ወረዳ ነዋሪዎችን ለብዙ እንግልት ሲዳርግ የነበረው የሆስፒታል ጥያቄ ምላሽ አግኝቶ ዛሬ ላይ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑ ለነዋሪዎች እፎይታ የሰጠ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ፓርቲው የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የገጠር መንገድ ተደራሽ እያደረገ ይገኛል ያሉት የሰልፉ ታዳሚዎች በከተማዋ የተጀመረው ንፁህ የመጠጥ ውሃ ግንባታ እና የጎሬ ማሻ ቴፒ የኮንክሪት አስፓልት መንገድ ፕሮጀክት እንዲጠናቀቅ ፓርቲው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ሲሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ያሉት የሰልፉ ታዳሚዎች፤ የጀመረውን ፕሮጀክት እንዲያጠናቅቅና የሀገራችን ሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲያስቀጥል በያዝነው ካርድ ድምፃችንን በመስጠት የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
የፀና ሰላም፣ የቀና ስርዓት፣ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!፣ ብልጽግናን ይምረጡ እና የምርጫ ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው የሚሉ መፎክሮችን በመያዝ በድጋፍ ሰልፉ ላይ ታድመዋል።
ዘጋቢ፡ ወንድማገኝ ገሪቶ – ከማሻ ጣቢያችን

More Stories
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያካሂደው አለም አቀፍ ኮንፍረንስ ጀመረ
የበቆሎ ምርጥ ዘር በወቅቱ በማግኘታቸው ትኩረታቸውን የእርሻ ዝግጅት ላይ እንዲያደርጉ እንዳስቻላቸው በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ
ከወላይታ ዞንና ሶዶ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የወጣቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች በወላይታ ሶዶ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፍ አድርገዋል