የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያካሂደው አለም አቀፍ ኮንፍረንስ ጀመረ
የዩኒቨርስቲው ፕሬዝደንት ዳዊት ሀዬሶ ዶ/ር በመግቢያ ንግግራቸው ወቅት እንደገለፁት የሰላም አምባሳደር የሆነው የዋቸሞ የዩቨርሲቲ ከመማር ማስተማር በተጨማሪ በማህበረሰብ አገልግሎት ብሎም በምርምርና ጥናት ስራዎች ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አመላክተዋል።
ዩኒቨርሲቲውን የምርምር ማዕከል ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ፕሬዝደንቱ፥ ዩኒቨርሲቲው ከዋና ማዕከሉ በተጨማሪ ባሉት ካምፓሶቹ በሁሉ አቀፍ ዘርፎች በርካታ ልማታዊ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ኮንፈረንሱ ከሚያዝያ 29-30/2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶን ጨምሮ የማኔጅመንት አባላትና የሥራ ኃላፊዎች፣ አለም አቀፍ ተመራማሪዎች ዳይሬክተሮችና እና ሌሎች እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛል።
ዘጋቢ: አማኑኤል አጤቦ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ