በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ኤጀንሲ Giz ከተሰኘ የጀርመን አለም አቀፍ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር በከምባታ ዞን በአንበርቾ ተራራ እና በጉራጌ ዞን በአረቅጥ ሀይቅ አሳታፊና የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ዙሪያ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የህልውና መሠረት የሆነውን የመሬት ገጽታና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን የመጠበቅና መንከባከብ ኃላፊነት የማህበረሰቡ እና የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊሆን እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የመሬት አሰተዳደር እና አጠቃቀም ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ አብዱልአፊዝ ሀሰን፣ የፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር እና የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ የጀርመን አለም አቀፍ የልማት ድርጅት አማካሪ አቶ አንተነህ ወንድሙ እና ተወካዮች እንዲሁም የማህበረሰብ ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ ኤርጡሜ ዳንኤል እና መልካሙ ታፈሰ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
በዓልን ምክንያት በማድረግ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው
ጥራት ያለው ቡና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሚናው የጎላ መሆኑን በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ