ከወላይታ ዞንና ሶዶ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የወጣቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች በወላይታ ሶዶ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፍ አድርገዋል
በሰልፉ የተገኙት የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ አፀደ አይዛ፤ ወጣቱ የብልፅግና ዕሳቤን በመያዝ አሰባሳቢ ገዢ ትርክትን ለመገንባት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣና የኢትዮጵያ ሰላምንና አንድነትን ማጽናት እንደሚገባው አሳስበዋል።
ወጣቱ ግንቦት ወር የሚካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ ምርጫ ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶን በመምረጥ ሀገርን እንዲያስቀጥሉና እንዲያፀኑ ጥሪ አቅርበዋል።
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ወጣቱ ንቁ ተሳታፊ በመሆኑ ብልፅግናን እንዲመርጡና የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።
ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶችን የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም በበኩላቸው፤ ወጣቶች 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በታቀደው መሠረት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸው ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል።
ሀገር የምትገነባውና ህልውናዋ የሚጸናው በወጣት ኃይል ተሳትፎ መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ እታገኝ፤ ወጣቶች 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በንቃት መሳተፍ ብቻ ሳይሆን ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ በቀሌች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
የባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ አመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል
የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምክር ቤቶች ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባቸው የኮንሶ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ገለጸ
የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ አሳታፊ እና የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ