ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የዜጎችን የመልማት ፍላጎት ደረጃ በደረጃ በመመለስ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ ተገለጸ
በጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲን በመወከል የክልል ምክር ቤት ዕጩዎችን የማስተዋወቅና የምርጫ ቅስቀሳ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የጎፋ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪና የፖለቲካ እና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቦረና ቦላዶ፤ የለውጡ መንግስት ዜጎች በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካው ዘርፍ ራሳቸውን እንዲችሉ ያስቻለ ጠንካራ ፓርቲ በመሆኑ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል በምርጫው ንቁ ተሳታፊ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።
የህብረተሰቡን የመልማት ፍላጎት ለማሟላት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ግብርናን ወደ ዘመናዊ እርሻ በማሸጋገር ከውጪ የሚገባውን የስንዴ ምርት በሀገር ውስጥ በማምረት የሀገር ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ ያስቻለ ጠንካራ ፓርቲ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ማስቀጠል ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያዕቆብ ደበላ፤ የለውጡ መንግስት በሁሉም ዘርፍ እያስመዘገበ ያለውን ለውጥ ለማስቀጠል በሰላም፣ በፍቅር እና በአንድነት በመያያዝ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል ፓርቲውን በመምረጥ የራሳቸውን ሀላፊነት መወጣት እንደሚገባቸው አስረድተዋል።
በየአካባቢው ከህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የዘለቀውን የጤና፣ የመንገድ እና የተለያዩ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን በመመለስ ለውጥ እያስመዘገበ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑን አንስተው፤ ይህንን ለማስቀጠል ብልጽግና ፓርቲን መምረጥ የነገዋን የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የደምባ ጎፋ ምርጫ ክልል አንድን በመወከል ለክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪዎች ከአባላቱ እና ከደጋፊዎች ጋር የትውውቅና ቅስቀሳ መርሃ-ግብር አድርገዋል።
ዘጋቢ፡ ምህረት መርዕድ – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
በመንግስት ድጋፍና በህብረተሰቡ ተሣትፎ የተገነባው ጤና ጣቢያ በጎፋ ዞን ደንባ ጎፋ ወረዳ ወይዴ ውርኪ ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
የሳውላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ወንጀልን የሚጸየፉ አምራች ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለፀ
በዳውሮ ዞን ገና ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳና የፓርቲ ምርጫ ምልክት የማስተዋወቅ መርሃ ግብር ተካሄደ