አርሰናል ከ20 ዓመታት በኋላ በሻምፒዮንስ ሊጉ ለፍፃሜ ደረሰ
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን በድምር ውጤት 2ለ1 በማሸነፍ ከ20 ዓመታት በኋላ ለፍፃሜ ደርሷል።
በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው የመልስ ጨዋታ መድፈኞቹ 1ለ0 አሸንፈዋል።
የአርሰናልን ወሳኝ የማሸነፊያ ጎል ቡካዮ ሳካ በ44ኛው ደቂቃ አስገኝቷል።
ቡካዮ ሳካ በኤምሬትስ ስታዲየም በተደረጉ 14 የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ በ14 ጎሎች ላይ በቀጥታ ተሳትፎ አድርጓል፤ ዘጠኝ ጎሎችን ሲያስቆጥር አምስት ደግሞ አመቻችቶ አመቻችቶ አቀብሏል።
በአጠቃላይ በ28 የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች 13 ጎሎችን እና ስምንት አሲስቶችን አስመዝግቧል።
ባለፈው የውድድር ዘመን በፒኤስጂ ላይ ካስቆጠረው ጎል በመቀጠል፣ በሁለት የተለያዩ የቻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ ጎል ያስቆጠረ የመጀመሪያው የአርሰናል ተጫዋች ሆኗል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዘንድሮ በሻምፒዮንስ ሊጉ በ14 ተከታታይ ጨዋታዎች ሳይሸነፍ በሀንጋሪ ቡዳፔስት በፑሽካሽ አሬና ለሚካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ መድረስ ችሏል።
አርሰናል በፍፃሜው ከባየርንሙኒክ እና ፒኤስጂ አሸናፊ ጋር የሚፋለም ይሆናል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
የአርሰናል የ20 ዓመታት የፍፃሜ ጥበቃ በቡዳፔስት ያበቃል!
አርባምንጭ ከተማ መቀሌ 70 እንደርታን አሸነፈ
“ከማንችስተር ዩናይትድ ልወጣ እችል ነበር፤ ነገር ግን እዚህ ስኬታማ መሆን ትልቅ ትርጉም አለው”ብሩኖ ፈርናንዴዝ