አርባምንጭ ከተማ መቀሌ 70 እንደርታን አሸነፈ
በ30ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ አርባምንጭ ከተማ መቀሌ 70 እንደርታን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአዞዎቹን ወሳኝ የማሸነፊያ ጎሎች አብዱል ራህማን እና አሸናፊ ፊዳ አስገኝተዋል።
በአሰልጣኝ አዲሴ ካሳ የሚመራው አርባምንጭ ከተማ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
በውድድር ዓመቱ 5ኛ ድሉን ያሳካው አርባምንጭ ከተማ ምንም እንኳን ደረጃውን ባያሻሽልም ነጥቡን 28 በማድረስ ከመቀሌ 70 እንደርታ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 2 አጥቧል።
12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቀሌ 70 እንደርታ 30 ነጥቦችን ይዞ 19ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
አርባምንጭ ከተማ በቀጣይ ሳምንት በዱንጉዛ ደርቢ ከወላይታ ድቻ ጋር የሚጫወት ይሆናል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ሪያል ማድሪድ ያን ዲዮማንዴን በታሪካዊ የዝውውር ክፍያ አስፈረመ
ብሩኖ ጊማሬስ የሕክምና ምርመራውን በስኬት አጠናቀቀ
9 ክለቦች በአዲስ አሰልጣኞች ፍልሚያቸውን የሚጀምሩበት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ