ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ የቡና ኮንፈረንስ ተጠናቋል
በቡና ላይ ከፍተኛ ጥናትና ምርምር ያደረጉ አለም አቀፍ የቡና ሳይንስ ተመራማሪዎች ጥናታዊ ጽሑፋቸውን አቅርበዋል።
ጥናታዊ ጽሑፉን ተከትሎ የቡና ልማትንና የግብይት ሥርዓትን በማሳለጥ የአምራቹን ህብረተሰብ ሕይወት ለመለወጥ በሚያስችሉ ተግባራት መሰራት እንዳለባቸው የኮንፈረሱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
በተመራማሪዎችና በአምባሳደሮቹ የወሺ ግሪን ኮፊ ቡና ልማት ጉብኝት የተደረገ ሲሆን ጎብኝዎቹም ባዩት የቡና ልማት እንክብካቤና የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ ሥራዎች መደሰታቸውን አስረድተዋል።
በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ የሚገኘው የቦንጋ ብሔራዊ የቡና ሙዚየም ጉብኝት ተደርጓል።
በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የሚገኘዉ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቡና ላብራቶሪ ጉብኝት ሲደረግ አጠቃላይ የላብራቶሪ አገልግሎት አሰጣጡን በተመለከተ የቡና ሳይንስ ተመራማሪው ዶ/ር ክፍሌ በላቸው ገለጻ አድርገዋል።
የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ክፍሌ ወ/ሚካኤል፣ የቦርዱ አባል ዶ/ር ተክለአብ ቡሎና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ደጌላ ኤርጌኖ የማጠቃለያ መድረኩን የመሩ ሲሆን፤ ከቀረበው ምርምር ግኝትም ሆነ ከተሳታፊዎች አስተያየት ለቀጣይ ሥራዎች አጋዥ የሚሆኑ ግብዓቶች እና ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገራት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን የሚያጠናክሩ ጉዳዮች መገኘታቸውን ተናግረዋል።
የጥናትና ምርምር ሥራዎቻቸውን ላቀረቡት ተመራማሪዎችና አስተባባሪዎች የምስጋናና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ደጌላ ኤርገኖ አያይዘውም፤ የዓለም ዓቀፍ የቡና ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ መደረጉ አበርክቶው የላቀ መሆኑን ገልጸው ኬት ኮፊ/KET COFFEE/ ከተባለ ዓለም አቀፍ ካምፓኒ ጋር የውል ስምምነት ተፈራርመዋል።
በቦንጋ አለም አቀፍ የቡና ኮንፈረስ ላይ ከፍተኛ ጥናትና ምርምር ያደረጉ አለም አቀፍ የቡና ሳይንስ ተመራማሪዎች፣ አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የካፋ ንጉስና ምክረቾ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
ዘጋቢ፡ መለሠ ገብሬ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
የባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ አመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል
የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምክር ቤቶች ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባቸው የኮንሶ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ገለጸ
የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ አሳታፊ እና የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ