የሀይማኖት ተቋማት በመተባበር እና በመነጋገር ለሀገር ግንባታ በጋራ ልንሰራ ይገባል – የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ
ሀዋሳ: ሚያዚያ 25/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሀይማኖት ተቋማት በመተባበር እና በመነጋገር ለሀገር ግንባታ በጋራ ልንሰራ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ገለጹ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የሰላ፣ የልማትና ብልፅግና ማዕከል ለማድረግ ሙስሊሙ ማህበረሰብ አይተኬ ሚና እንዳለው ተመልክቷል።
በኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በአርባምንጭ ከተማ በይፋ ተመስርቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሀጂ ያሲን ከድር የምክር ቤቱ መቋቋም ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሙስሊም ወጣቶች አንድነትና ማህበራዊ ዕሴት ግንባታ አበርክቶው ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል ።
የአርባምንጭ ከተማ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሚተገበሩበት የብልፅግና እና የለውጥ ከተማ መሆኗን ያወሱት የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ መስፍን መንዛ (ዶ/ር)፥ መንግስት በሁለም የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በጋራ ይሰራል እየሰራም ይገኛል።
በሀገራችን የተጀመሩ የልማት ተግባራትን ከመደገፍ ባሻገር የሙስሊም መለያ የሆነውን ሰላም አጠናክረን እናስቀጥል ሲሉ አሳስበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተወካይና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ዘውዴ፥ መንግስት ክልሉን የሰላም፣ የልማትና ብልፅግና ማዕከል ለማድረግ እያከናወነ ለሚገኘው ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ ሙስሊሙ ማህበረሰብ አይተኬ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
መንግስት ከሁሉም ሀይማኖቶች እኩል የሚሰራና ችግሮችን በአብሮነት የሚፈታ በመሆኑ የወጣቶች ካውንስል መቋቋም በቀጣይ ለሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ግብዓት እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፥ መንግስት ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እየሰጠ ያለው ድጋፍ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው የወጣቶች ካውንስል መመስረት ለሀገር ግንባታ ለሰላምና ልማት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ወጣቱ የስጋት ሳይሆን የልማት ነው ያሉት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ሀገራችን የሁሉም እምነት እናትም አባትም ናትና ሁሉም የሀይማኖት ተቋማት በመተባበር እና በመነጋገር ለሀገር ግንባታ በጋራ ልንሰራ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ጫፍ የወጣ ፅንፈኝነትንና አክራሪነትን ትተን የጋራ በሆነችው ሀገራችን በመፈቃቀድ፣ በመቻቻል እና በፍቅር በፅኑ መሰረት እናፅናት ብለዋል።
በመርሀ ግብሩ በአርባምንጭ ከተማ ለሚገነባው ሁለገብ የገበያ ማዕከል ህንፃ ግንባታ መሰረት የማኖር ስነስርዓት የተከናወነ ሲሆን በመጨረሻም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በይፋ ተመስርቷል ።
ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
ባህላዊ እሴትና የወንድማማችነት ትስስርን የሚያድስ የ“ኦዴ ኦሶ” ቤተሰብ ምረቃ ስነ-ስርዓት በልዩ ድምቀት ተካሄደ
የጎፋ ዞን ልማት ማህበር ሥራ አመራር ቦርድ የ3ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሄደ
የምሁራን አንድነትን ማጠናከርና የእርስ በእርስ መከባበር ባህልን ማጎልበት ለአካባቢው ዘላቂ ሠላም መስፈን ወሳኝነት እንዳለው ተመላከተ