በብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስተባባሪዎችና ዕጩ ወኪሎች ኃላፊነትና ግዴታ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
በብልጽግና ፓርቲ ወኪሎች ኃላፊነትና ግዴታ ላይ ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ሥልጠና ተሰጥቷል።
በምርጫው ሂደት የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ አስተባባሪዎችና የዕጩ ወኪሎች ሥራ ውጤታማ እንዲሆን በጌጫ ከተማ ላይ ለተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ሥልጠና ተሰጥቷል።
በምርጫ ወቅት የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስተባባሪዎችም ሆኑ የዕጩ ወኪሎች መብታቸውንና ግዴታቸውን በምርጫ ቦርዱ በተቀመጠው የአፈፃፀም መመሪያ መሠረት መወጣት እንዳለባቸው ተብራርቷል።
ምርጫው ፍትሐዊ፣ ተዓማኒና ዲሞኪራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የአባላቱን ርብርብ እንደሚጠይቅ የገለፁት የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ፤ ከምርጫው ሂደት ጀምሮ እስከ ማጠቃለያ የምርጫ ሥርዓቱ በጥንቃቄ መመራት እንዳለበት አሳስቧል።
በሥልጠናው የክልል፣ የዞንና የወረዳ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ተሳታፊ መሆናቸውን የአንድራቻ ወረዳ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ