ከሚያዝያ 22 ጀምሮ በጂንካ ከተማ ለሚስተናገደው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የመጨረሻ የዝግጅት ምዕራፍ ግምገማ መካሄዱን የክልሉ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከስታወቀ
ውድድሩን በስኬት ለማጠናቀቅ በቅንጅት እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት በጥንካሬ የተፈተሹ መሆናቸውንም ነው ፌደሬሽኑ ያስታወቀው።
ከነገ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጂንካ ከተማ ለሚጀመረው የክልል ክለቦች ሻምፒዮና የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በክልሉ እግር ኳስ ፌደሬሽንና በዞኑ የስፖርት ምክር ቤት በጋራ ተገምግመዋል።
ውድድሩን ለማስተናገድም በየደረጃው በተዋቀሩ አካላት የተደረጉ ጥረቶችን በጥንካሬ የተመለከታቸው መሆኑን ነው የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ደመላሽ ይትባረክ የገለጹት።
ከ20 በላይ ክለቦች የሚሳተፉበት ውድድር ለቀጣይ 15 ቀናት እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
የማህበረሰቡ ስፖርት አፍቃሪነትና የአካባቢው ምቹ ሁኔታ ውድድሩን በከተማው ለማስተናገድ ምክንያት እንደሆነ የፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወልደሚካኤል መስቀሌ ገልጸዋል።
ለዚህም አስፈላጊው የቴክኒክ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
ውድድሩ ለከፍተኛ የውድድር መድረኮች የሚመጥኑ ስፖርተኞች እንደሚመረጡበትም አስረድተዋል።
የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም አታ በበኩላቸው፤ እንግዶች እየገቡ መሆኑን ጠቅሰው ስፖርቱን ለማስተናገድ አስፈላጊ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል።
ይህም በክልሉ የእግር ኳስ ፌደሬሽን በኩል እውቅና የተሰጠው መሆኑንም ተናግረዋል።
በተቀናጀ የጸጥታ አካላት ጥምረት ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እየተሰራ እንደሆነ የገለጹት ደግሞ የኣሪ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር መሰለ ገብሬ ናቸው።
ማህበረሰቡም በተለመደ ጨዋነት ውድድሩን እንዲከታተል ጥሪ ቀርቧል።
ዘጋቢ: ወንድሜነህ አድማሱ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ