ካይ ሀቨርትዝ ከጉዳቱ በቶሎ የማገገም ተስፋ አለው
አርሰናል በሳምንቱ መጨረሻ ከኒውካስል ጋር በነበረው ጨዋታ የጡንቻ ጉዳት ያስተናገደው ካይ ሀቨርትዝ፣ ለዋንጫ በሚደረገው ወሳኝ የውድድር ማጠናቀቂያ ላይ ለቡድኑ ግልጋሎት ይሰጣል የሚል ተስፋ አለው።
ይህ የ 26 ዓመቱ ጀርመናዊ አጥቂ፣ ቡድኑ በኤዲ ሀው ስብስብ ላይ ድል ባስመዘገበበት የቅዳሜው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ በደረሰበት የጭን እግር ህመም ምክንያት ሜዳውን ለቆ ለመውጣት ተገዷል።
ክለቡ ተጫዋቹ ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ግልጽ የሆነ የጊዜ ገደብ ባያስቀምጥም፣ አርሰናል ከ 2004 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ለማንሳት በሚያደርገው ጥረት በሊጉ ቀሪ አራት ጨዋታዎች ላይ ሀቨርትዝ ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል።
የሚኬል አርቴታ ስብስብ በሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ላይም የሚገኝ ሲሆን፣ በነገው እለት ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።
ሀቨርትዝ በዚህ የውድድር ዘመን በጉልበት ጉዳት ምክንያት ለስድስት ወራት ያህል ከሜዳ ርቆ የነበረ ሲሆን፣ ከጥር ወር ጀምሮ ወደ ጨዋታ ከተመለሰ በኋላ ባደረጋቸው 19 ጨዋታዎች 5 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ