ማኑኤል ኖየር፣ በባየር ሙኒክ እስከ 2027 ለመቆየት ተስማማ
የባየር ሙኒክ እና የጀርመን እግር ኳስ ምልክት የሆነው አንጋፋው ግብ ጠባቂ ማኑኤል ኖየር፣ በክለቡ ያለውን ቆይታ እስከ ሰኔ 2027 ለማራዘም መስማማቱ ተረጋግጧል።
ይህ ስምምነት ኖየር በባየር ሙኒክ ቤት እስከ 41 ዓመቱ ድረስ እንዲቆይ የሚያደርገው ሲሆን፣ በክለቡ ታሪክ ውስጥ ያለውን ድንቅ አሻራ ይበልጥ የሚያጸና ሆኗል።
ማኑኤል ኖየር ይህንን አዲስ ውል በመፈረም በባየር ሙኒክ ቤት ለ16ኛ ተከታታይ የውድድር ዘመን ለመሰለፍ ዝግጁ ሆኗል።
እ.ኤ.አ. በ2011 ከሻልካ 04 ክለቡን የተቀላቀለው ኖየር፣ አሁንም ድረስ በዓለም እግር ኳስ ካሉ ምርጥ ግብ ጠባቂዎች ተርታ መሰለፉን ቀጥሏል።
በአሊያንዝ አሬና በቆየባቸው ዓመታት ኖየር ያስመዘገባቸው ድሎች “ለማመን የሚከብዱ” ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም።
ሁለት ጊዜ የአውሮፓ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን ሁ (2013 እና 2020) እንዲሁም ለ11 ተከታታይ ዓመታት የጀርመን ቡንደስሊጋ ሻምፒዮን መሆን ችሏል።
“ዘመናዊ ግብ ጠባቂ” (Sweeper-Keeper) የሚለውን ትርጉም ለዓለም ያስተዋወቀና ለበርካታ ዓመታት የዓለም ምርጥ ግብ ጠባቂ ተብሎ የተመረጠ ነዉ።
ይህ የውል ማራዘም ባየር ሙኒክ በቀጣይ ዓመታት ለሚገነባው ወጣት ስብስብ ልምድና መሪነትን እንደሚሰጥ ይታመናል።
ኖየር ከከባድ ጉዳቶች አገግሞ ወደ ቀድሞ ብቃቱ መመለሱ፣ ክለቡ አሁንም በእሱ ላይ ሙሉ እምነት እንዲጥል አድርጎታል።
ባየርን ሙኒክ በዘንድሮው የውድድር ዘመን የቡንደስሊጋው ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን በዲኤፍ ኤል ለፍፃሜ በመድረሱ እንደ በሻምፒዮንስ ሊጉ የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑን በማረጋገጥ የሦስትዮሽ ባለድል ለመሆን በመገስገስ ላይ ይገኛል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ቡካዮ ሳካ እና ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለኒውካስል ጨዋታ ወደ ቡድኑ የመመለስ ‘እድል’ አላቸው” – ሚኬል አርቴታ
“እዚህ መሆን ደስ ይለኛል!” – ማይክል ካሪክ
ማቲያስ ዴሊኽት ወደ ሜዳ ለመመለስ ልምምድ ጀመረ