የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ(ዶ/ር) መጭው ጊዜ ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ብርሃን የምንሸጋገርበት ብሩህ ዘመን መሆኑን ተናገሩ
ሚኒስትሩ በጎፋ ዞን ከገዜ ጎፋ ወረዳ እና ከቡልቂ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
ሚኒስትሩ ከነዋሪዎቹ ጋር በልማት፣ መልካም አስተዳደር እና በምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነዋሪዎቹ ብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር ፓርቲ በመሆኑ በአካባቢያቸው በርካታ ለውጦች መታየታቸውን ጠቁመው፤ በመንገድ፣ መብራትና ውሃ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚታዩ ውስንነቶች በቀጣይ በትኩረት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ፤ ብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያን ከድህነትና ኋላቀርነት በማላቀቅ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ያለ ፓርቲ በመሆኑ ለውጡን ማስቀጠል ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ በበኩላቸው፤ ጎፋን የለውጥ እና የብልጽግና ማዕከል ለማድረግ ብልጽግና ፓርቲ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በመሰረተ ልማት ተደራሽነት ላይ የሚታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ መንግስት በትኩረት ለመስራት መዘጋጀቱን አብራርተዋል።
በኢፌዲሪ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ(ዶ/ር) ከለውጥ ወዲህ በአካባቢው የሚዳሰስና የሚጨበጥ ለውጥ እየታየና የህዝቡ ተጠቃሚነት እየተጠናከረ ሲሆን ይህንን ለውጥ ብልጽግና ፓርቲ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
መንግስት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር ለማድረግ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት እየተረባረበ ሲሆን የሁሉም ዜጎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በህዝቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲጠናቀቅ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ ወደ ቡልቂ ከተማ አስተዳደር ሲደርሱ በአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና በከተማው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
ከመማር ማስተማር ተግባር ባለፈ የአካባቢ ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የሚዛን ግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ አስታወቀ
በተቀሩት አጭር ቀናት ህብረተሠቡ የመራጭነት ካርዱን በመውሰድ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳና አካባቢው የፌደራልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ አቀረቡ
ማህበራዊ ሚዲያ ጊዜና ቦታ ሳይገድበው መረጃን በፍጥነት ተደራሽ ስለሚያደርግ ተጠቃሚዎች ትክክለኛ እና ተአማኒነት ያለውን መረጃ ማሰራጨት ይጠበቅባቸዋል – ዶ/ር በኃይሉ ገ/ማሪያም