በተቀሩት አጭር ቀናት ህብረተሠቡ የመራጭነት ካርዱን በመውሰድ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳና አካባቢው የፌደራልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ አቀረቡ
ከፍተኛ አመራሮቹ የመሎ ኮዛ ወረዳን በመወከል ለፌደራልና ለክልል ምክር ቤቶች በሚወዳደሩባቸው ምርጫ ክልሎች በመገኘት የመራጭነት ካርድ ወስደዋል።
በምርጫ ክልሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ኢንጂነር ካሳሁን ሰለሞንና የክልል ምክር ቤት ዕጩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማሩፋ መኩሪያ እንደገለጹት፤ በሀገር ደረጃ የተጀመረው የዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ከግብ እንዲደርስ ዕድሜዉ ለምርጫ የደረሰ ዜጋ ሁሉ በምርጫው አጠቃላይ ሂደት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ፣ የሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊና የምርጫ ጣቢያው የክልል ምክር ቤት ዕጩ አቶ ምናሴ ኤልያስ፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲን ለማፅናትና ኢትዮጵያዊ የመግባባት ዴሞክራሲን ለመትከል መሠረት የሚጣልበት በመሆኑ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
በጎፋ ባህልና ቋንቋ፣ ኪነ-ጥበባዊ ሥራው የሚታወቀው አርቲስት አለሙ አይሳ በበኩሉ የመራጭነት ካርዱን በተቀመጠው ጊዜ ገደብ መውሰዱን ገልጾ በየትኛውም የሙያ ዘርፍ የሚገኝ ዜጋ ካርድ በመውሰድ የመራጭነት መብቱን መጠቀም እንደሚገባው ገልጿል።
የምርጫ ካርድ የወሰዱ የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው የፊታችን ሰኞ መጋቢት 28/2018 ዓ.ም በሚጠናቀቀው የመራጮች ምዝገባ በሁሉም አካባቢዎች ሕብረተሰቡ በነቂስ በመዉጣት የመራጭነት ካርድ እንዲወስድ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን
በምርጫዬ የሞባይል መተግበሪያ ባሉበት ሆነው ራስዎን ለመራጭነት ይመዝግቡ!
ምርጫዬ ለአንድሮይድ፦ https://play.google.com/store/apps/details…
ምርጫዬ ለአፕስቶር፦ https://apps.apple.com/us/app/mirchaye/id6756587049
ምርጫዬ ለድረ-ገጽ:- https://mirchaye.portal.nebe.org.et/
#እመዘገባለሁ #እሳተፋለሁ

More Stories
በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚገነባው የእንስሳት ግብይት ማዕከል ግንባታ የሳይት ርክክብ ተደረገ
የሀገራችንን ብልፅግና እውን ለማድረግ በበቂ ዕውቀትና ክህሎት የታነፁ ምሁራንን በማፍራት የተሻለ ትውልድ መቅረጽ ቁልፍ ተግባር ነው ሲሉ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) ገለፁ
ተፈላጊነቱ እየጨመረ የመጣውን የቆጮ ምግብ ጥራትና ተደራሽነት ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎች እያከናወነ መሆኑን በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የብሔራዊ ግብርና ባዮ ቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል ገለጸ