በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 25 ሺህ 338 ሊትር ቤንዝልና 62 ሺ 686 ሊትር ናፍጣ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ
ከነዳጅ እጥረት ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን ህገ-ወጥ የግብይት ስርዓት ለመቆጣጠር ጠንካራ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ቢሮው አረጋግጧል፡፡
ቢሮው ከነዳጅ እጥረት እና ከህገ-ወጥ የግብይት ስርዓት ጋር ተያይዞ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን በመግለጫቸው እንዳሉት፤ የነዳጅ ስርጭትና ግብይት ስርአትን ለመቆጣጠር እንዲያችል ጠንካራ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ በክልሉ በ12 ዞኖችና በ 3ቱ ሪጂዮ ፖሊ ከተሞች እየተሠራ ይገኛል።
ከዚህ አኳያ ፖሊስን ጨምሮ ከግብረ ሀይሉ ጋር በመሆን እስከታችኛው መዋቅር በተደረገው የቁጥጥር ስርዓትና ድንገተኛ ፍተሻ 25 ሺህ 338 ሊትር ቤንዝልና 62 ሺ 686 ሊትር ናፍጣ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።
በዚህ ህገ-ወጥ የግብይት ስርአት ውስጥ የተሳተፉ አራት የንግድ ባለሙያዎች በህግ እየተጠየቁ ሲሆን ነዳጅ የሚያመላልሱና የሚያጓጉዙ 27 አካላትና 8 የማደያ ባለቤቶች በቁጥጥር ስር ውለው በህግ እየተጣራ መሆኑን ወ/ሮ ሰናይት አብራርተዋል።
በዚህ መነሻ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ውስጥ የገቡ ስምንት ማደያዎች መታሸጋቸውንም ጠቅሰዋል።
ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱን ለመቆጣጠር እንዲያስችል በአብዛኛው ማደያዎች የ CCtv ካሜራ እንዲያስገጥሙ የተሰራ መሆኑን አብራርተው፤ የተወሰኑ ማደያዎች ያላስገጠሙ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በክልሉ የሚገኙ 113 ማደያዎች በፍትሀዊ መንገድ ለተጠቃሚው ነዳጅ እንዲያደርሱ ጠንካራ ስራ እየተሰራ መሆኑን በመግለጫቸው አንስተዋል የቢሮው ኃላፊ።
ህገ-ወጥነቱን በመቆጣጠር ሂደት አጋዥ በመሆን ለሚመለከተው አካል ጥቆማ የሰጡ አካላት ሊመሰገኑ እንደሚገባና ይህ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመግለጫቸው አሳስበዋል።
ከነዳጅ አኳያ እንደ ሀገር የተቀመጠው አግባብ እንዲተገበር ሁሉም መረባረብ እንዳለበት አሳስበው፤ ለተግባራዊነቱም እንደ ቢሮ ጠንካራ ክትትል እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል ወ/ሮ ሰናይት።
ዘጋቢ፡ ማርታ ሙሉጌታ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 25 ሺህ 338 ሊትር ቤንዝልና 62 ሺ 686 ሊትር ናፍጣ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ

More Stories
በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚገነባው የእንስሳት ግብይት ማዕከል ግንባታ የሳይት ርክክብ ተደረገ
የሀገራችንን ብልፅግና እውን ለማድረግ በበቂ ዕውቀትና ክህሎት የታነፁ ምሁራንን በማፍራት የተሻለ ትውልድ መቅረጽ ቁልፍ ተግባር ነው ሲሉ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) ገለፁ
ተፈላጊነቱ እየጨመረ የመጣውን የቆጮ ምግብ ጥራትና ተደራሽነት ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎች እያከናወነ መሆኑን በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የብሔራዊ ግብርና ባዮ ቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል ገለጸ