ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፍትህና የጸጥታ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ
የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸምና በቀጣይ የትኩረት መስኮች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።
የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ብላቴ፤ በዞኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለማስከበር፣ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማክበርና መብትና ጊዴታውን የሚያውቅ ህብረተሰብ ለመፍጠር በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።
በልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዩች ከቀረቡ 3 ሺህ 618 መዝገቦች 3 ሺህ 529 መዝገቦች በዐቃቤ ህግ የተለያየ አስተያየትና ውሳኔ የተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
መምሪያው በሙስና ወንጀሎች እና በታክስና ኢኮኖሚ ወንጀሎች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ህጋዊ ውሳኔ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በዚህም ሊመዘበር የነበረ ከ11 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን ስለመቻሉ አብራርተዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፍትህና የጸጥታ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ሚና የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።
በመምሪያው ታክስና ኢኮኖሚ ወንጀሎች ዋና ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ደምሴ ዳይዶ እና የሴቶችና ህጻናት ልዩ ምርመራና ክስ ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ ትርፌ በጋራ እንደገለጹት፤ የህዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የፍትህ ተደራሽነትን ለማሳደግ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ አስረድተዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ዋና ኢንስፔክተር ታረቀኝ አጥናፉ፣ አቶ የንገረ የደና እና ኢንስፔክተር ውብነህ ደመላሽ፤ ፈጣንና ቀልጣፋ የፍትህ አገልግሎት ለህብረተሰቡ በመስጠት የሚፈጠሩ ችግሮችን በጋራ ለማረምና ተጠያቂነትን ለማስፈን የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መክረዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ ግንቦት 24 የሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚገነባው የእንስሳት ግብይት ማዕከል ግንባታ የሳይት ርክክብ ተደረገ
የሀገራችንን ብልፅግና እውን ለማድረግ በበቂ ዕውቀትና ክህሎት የታነፁ ምሁራንን በማፍራት የተሻለ ትውልድ መቅረጽ ቁልፍ ተግባር ነው ሲሉ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) ገለፁ
ተፈላጊነቱ እየጨመረ የመጣውን የቆጮ ምግብ ጥራትና ተደራሽነት ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎች እያከናወነ መሆኑን በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የብሔራዊ ግብርና ባዮ ቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል ገለጸ