የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በክልሉ ለሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ (CALM P for R) ፕሮጀክት ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በክልሉ ለሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
በአየር ንብረት አፈፃፀም የመሬት አያያዝ ፕሮግራም “Climate Action through Landscape Management” በዋናነት በዓለም ባንክ ድጋፍ የሚተገበር ሲሆን ግቡም የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ሥርዓት መዘርጋት መሆኑ ተመላክቷል።
የመድረኩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የተፈጥሮ ሀብት፣ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ውብሸት ዘነበ፥ ስልጠናው በቀጥታ ከማህበረሰቡ ህይወት ጋር በሚገናኙ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ያተኩራል ብለዋል።
በመሬት አጠቃቀምና በተፋሰስ ልየታ ስራዎች ላይ በፕሮጀክቱ የሚሰሩ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን አመልክተው፥ በአግባቡ መከታተል ከሰልጣኞች እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
በግብርናው ዘርፍ በተለይም የመሬት እና የአየር ንብረት መረጃ አያያዝ ስርዓትን ለማዘመን እንደሚያስችል ገልጸው፥ በዚህ ዘርፍ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን የግብርና ሚኒስቴር እየደገፈ በመሆሆ አመስግነዋል።
ስልጠናው ወደ ተግባር ሲቀየር ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚተገበር እንደሆነ ተናግረዋል።
የስልጠና መድረኩ ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፥ ከወረዳ እስከ ክልል መዋቅሮች የሚገኙ የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ ክፍሌ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው