አትሌት ንግስት ጌታቸው ለግማሽ ፍፃሜ ውድድር አለፈች
በዛሬው ዕለት በፖላንድ ቶሩን ከተማ መካሄድ በጀመረው 21ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር አትሌት ንግስት ጌታቸው ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፋለች።
በምድብ አራት ተደልድላ ውድድሯን ያከናወናችው አትሌት ንግስት 2 ደቂቃ ከ 02 ሴኮንድ ከ89 ማይክሮሴኮንድ በሆነ ሰዓት ርቀቱን በቀዳሚነት አጠናቃለች።
አትሌት ንግስት ጌታቸው ባለፈው ዓመት በቻይና ናንጂንግ በተካሄደው 20ኛው የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በሴቶች 800 ሜትር ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ ማሸነፏ የሚዘነጋ አይደለም።
የ800 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ ውድድር በነገው ዕለት የሚካሄድ ይሆናል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ