ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
በ34ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን 1ለ0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።
ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን በመጀመሪያው አጋማሽ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ጎል አስገኝቷል።
ሲዳማ ቡና በዚህ ዓመት 17ኛ የሊግ ድሉን ሲያሳካ አዳማ ከተማ በአንፃሩ 11ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
ሲዳማ ቡና ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 61 በማድረስ ከተከታዩ መቻል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 8 አስፍቷል።
አዳማ ከተማ በበኩሉ 39 ነጥቦችን ይዞ በወራጅ ቀጠናው አፋፍ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።